አበበች ሴቷ አሽከርካሪ
Dawit Girma
Yirgalem Birhanu

ባጃጅ ለመጓጓዣነት የምታገለግል አነስተኛ ባለ ሶስት ጎማ ተሽከርካሪ ናት፡፡

1

በማህበረሰባችን አሽከርካሪነት ወንዶች የሚበዙበት የስራ ዘርፍ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሴቶች አይሳተፉበትም፡፡

2

ከእለታት አንድ ቀን አበበች የመንጃ ፈቃድ ለመማር ገንዘብ ከቤተሰቦቿ ጠየቀች፡፡

ቤተሰቦቿም "ይሄማ ለሴት ልጅ ጥሩ አይደለም ሰውስ ምን ይላል?" አሏት፡፡

3

እሷ ግን "ሰው የሚሰራውን ሁሉ እንደማንኛውም ሰው የመስራት አቅም አለኝ" አለች፡፡ አሳመነቻቸው፡፡

4

ስልጠናውንም በሚገባ ተከታትላ አጠናቀቀች፡፡ ቤተሰቦቿም ምን እናርግላት ብለው ተማከሩ፡፡

5

ከዚያም ባጃጅ ሊገዙላት ወሰኑ፡፡ አበበችም በደብረ ብርሃን ጎዳናዎች ላይ ባጃጅ መንዳት ጀመረች፡፡

6

ከእለታት በአንድ ቀን አንድ ግሩም ሃሳብ ወደአዕምሮዋ መጣላት፡፡ ከባጃጇ ጀርባ ላይ ስልክ ቁጥሯ የታተመበት ትልቅ ማስታወቂያ ለጠፈች፡፡

7

ማስታወቂያው እንዲህ ይላል፡- "ነፍሰ ጡር ሴቶችን፣ አራስ እናቶችን፣ እና ህጻናትን በነፃ እናደርሳለን"፡፡

ከዚያም የሚወልዱ ሴቶችና ልጃቸውን ያመመባቸው እናቶች ወደ አበበች ይደውላሉ፡፡

8

በባጃጇ እየሰራች ገንዘብ አፈራች፡፡ በጎ ስራዋን መስራትም ቀጠለች፡፡ በቂ ገቢ የሌላቸው ድሃዎችንም በነፃ ማገልገል ያዘች፡፡

9

በዚህ ስራዋም አበበች በገንዘብ የማይታመን እርካታን አገኘች፡፡ ትላልቅ ሰዎችም መረቋት፡፡ በህጻናት እና በወላጆች ዘንድም በጣም ተወዳጅ ሰው ሆነች፡፡

አበበች ‹‹መልካም መስራት ለራስ ነው›› ትላለች፡፡

10
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አበበች ሴቷ አሽከርካሪ
Author - Dawit Girma
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Yirgalem Birhanu
Language - Amharic
Level - First paragraphs