አበበች ሴቷ አሽከርካሪ
Dawit Girma
Yirgalem Birhanu

ባጃጅ ለመጓጓዣነት የምታገለግል አነስተኛ ባለ ሶስት ጎማ ተሽከርካሪ ናት፡፡ ከተማ ውስጥ ከቦታ ቦታ በቶሎ ለመድረስ ታገለግላለች፡፡

1

ሴቶች እንደአሽከርካሪነት ያለ በብዛት ወንዶች ብቻ የሚሳተፉበት ሙያ ላይ አይሰማሩም ነበር፡፡

2

ከእለታት አንድ ቀን አበበች የመንጃ ፈቃድ ለመማር ገንዘብ ከቤተሰቦቿ ጠየቀች፡፡

ቤተሰቦቿም "ይሄማ ለሴት ልጅ ጥሩ አይደለም ሰውስ ምን ይላል?" አሏት፡፡

3

እሷ ግን "ሰው የሚሰራውን ሁሉ እንደማንኛውም ሰው የመስራት አቅም አለኝ" አለች፡፡ አሳመነቻቸው፡፡

ወላጆቿ በሃሳቧ ተስማሙ፡፡ የመንጃ ፈቃድ ስልጠናውን እንድትጀምር ፈቀዱላት፡፡

4

ስልጠናውንም በሚገባ ተከታትላ አጠናቀቀች፡፡

ቤተሰቦቿም ምን እናርግላት ብለው ተማከሩ፡፡

5

ከዚያም ባጃጅ ሊገዙላት ወሰኑ፡፡

አበበችም በደብረ ብርሃን ጎዳናዎች ላይ ባጃጅ መንዳት ጀመረች፡፡

6

ከእለታት በአንድ ቀን አንድ ግሩም ሃሳብ ወደአዕምሮዋ መጣላት፡፡

ከባጃጇ ጀርባ ላይ ስልክ ቁጥሯ የታተመበት ትልቅ ማስታወቂያ ለጠፈች፡፡

7

ማስታወቂያው እንዲህ ይላል፡ "ነፍሰ ጡር ሴቶችን፣ አራስ እናቶችን፣ እና ህጻናትን በነፃ እናደርሳለን"፡፡

8

ከዚያም የሚወልዱ ሴቶችና ልጃቸውን ያመመባቸው እናቶች ወደ አበበች ይደውላሉ፡፡

እሷም በባጃጇ አሳፍራ በፍጥነት ወደሃኪም ቤት ታደርሳቸዋለች፡፡

9

በባጃጇ እየሰራች ገንዘብ አፈራች፡፡ በጎ ስራዋን በመስራትም ቀጠለች፡፡ በቂ ገቢ የሌላቸው ድሃዎችንም በነፃ ማገልገል ያዘች፡፡

10

በዚህ ስራዋም አበበች በገንዘብ የማይታመን እርካታን አገኘች፡፡ ትላልቅ ሰዎችም መረቋት፡፡ በህጻናት እና በወላጆች ዘንድም በጣም ተወዳጅ ሰው ሆነች፡፡

11

ልጆች! መልካም መስራት ለራስ ነው፡፡

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አበበች ሴቷ አሽከርካሪ
Author - Dawit Girma
Translation - Dawit Girma
Illustration - Yirgalem Birhanu
Language - Amharic
Level - First sentences