ጥንቸል እና አያ ጅቦ እህል አመረቱ
Mutugi Kamundi
Rob Owen

በድሮ ጊዜ፣ ጥንቸልና አያ ጅቦ ጓደኛሞች ነበሩ፡፡

1

ጥንቸልም አያ ጅቦን፣ “በል እንግዲህ አንድ ላይ ሆነን እንረስ” አለችው፡፡

2

ጥንቸል አንድ ሃሳብ አቀረበ፤ እርሱም በቆሎ እንዲዘሩና ስራውንም በጋራ እንዲሰሩ፡፡

3

ጥንቸል አያ ጅቦን “የእኔ ድርሻ የሆነው ወፎችን የማባረር ስራ ከባድ ነው” አለችው፡፡

4

አያ ጅቦም መሬቱን ብቻውን ለማረስ ተስማማ፡፡

5

አያ ጅቦ ብቻውን አረም በሚያርምበት ወቅት፣ ጥንቸል ያለስራ ቁጭ ብላ ታንጎራጉራለች፡፡

6

በቆሎው ሲደርስ፣ ጥንቸል ወፎችን በማባረር ይዝናና ጀመር፡፡

7

ጥንቸል፣ “እኔ ከመሬት በላይ አመረትኩ፣ አንተ ከመሬት በታች አመረትክ፡፡” አለ፡፡

8

ጥንቸል በቆሎውን ሁሉ ሰብስባ በጎተራ ከተተች፡፡

9

ጅብ ግን ከመሬት በታች ያለውን ስራስር ብቻ አገኘ፡፡

10

ወዲያውም አያ ጅቦ እንደተታለለ አወቀ፡፡ ተበሳጨም፡፡

11

በቀጣይ ድንች ሊያመርቱ አቀዱ፡፡ አያ ጅቦ፣ “ከመሬት በላይ አመርታለሁ” አለ፡፡

12

እያንጎራጎሩ ግብርናቸውን አብረው ይሰሩ ጀመር፡፡

13

በምርቱ ወቅት፣ አያ ጅቦ የድንቹን ቅጠል ብቻ ወሰደ፡፡

14

ጥንቸል ግን መአት ትላልቅ ድንቾች አመረተችና በጎተራ ውስጥ አከማቸች፡፡

15

አያ ጅቦም ተናዶ ጥንቸልን ሊበቀላት አሳደዳት፡፡ ጓደኝነታቸውም በዚያው አበቃለት፡፡

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጥንቸል እና አያ ጅቦ እህል አመረቱ
Author - Mutugi Kamundi
Translation - Dawit Girma
Illustration - Rob Owen
Language - Amharic
Level - First words