ዝንጀሮና ድርቁ
Alice Edui
Salim Kasamba

ዝናብ አልዘነበም ነበር፡፡ መሬቱም በጣም ደርቋል፡፡

1

ይቺ ዝንጀሮ ምግብና ውሃ ፍለጋ ከቤቷ ወጥታለች፡፡

2

ተራራውንና ሸለቆውን እያቆራረጠች ሄደች፡፡

3

ቲርኮል ከተባለ ስፍራም ደረሰች፡፡

4

ዝንጀሮ በዚህ ስፍራ ተደሰተች፡፡

5

ፍራፍሬ በልታ ወፈረች፡፡ ጓደኞቿ ግን ጠፉባት፡፡

6

ስለሆነም ዝንጀሮዋ ረጅም መንገድ ተጉዛ እቤቷ ደረሰች፡፡

7

ሌሎቹም ዝንጀሮዎች ሲያዩዋት ተደሰቱ፡፡

8

‹‹ይህ በፍራፍሬ የበለጸገ ስፍራ የት ነው ያለው?›› ሲሉ ጠየቋት፡፡

9

‹‹እወስዳችኋለሁ›› አለቻቸው፡፡

10

ሌሎቹም ዝንጀሮዎች ቲርኮልን ወደዱት፡፡ እዚያም በቋሚነት ለመኖር ወሰኑ፡፡

11

የቲርኮል ዝንጀሮዎች ግን ሃሳብ ገባቸው፡፡

12

‹‹እነዚህ አዲስ መጤ ዝንጀሮዎች ፍራፍሬያችንን በልተው ይጨርሱብናል›› በማለት ተጨነቁ፡

13

የቲርኮል ዝንጀሮዎች አዲሶቹን ዝንጀሮዎች ለማጥቃት ተነሱ፡፡

14

‹‹ለምን እንጣላለን?›› አሉ አንድ አዛውንት፡፡ ‹‹በቂ ፍራፍሬ እያለ!››

15

ይህም እውነት ነበር፡፡ ስለሆነም ዝንጀሮቹ በሰላም አብረው መኖር ጀመሩ፡፡

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ዝንጀሮና ድርቁ
Author - Alice Edui
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Salim Kasamba
Language - Amharic
Level - First words