ሰነፉ አናንሲ
Ghanaian folktale
Wiehan de Jager

አናንሲ ሰነፍ ሸረሪት ነበር፡፡

1

ምግብ ቢወድም ማዘጋጀቱን ግን ይጠላል፡፡

2

አናንሲ ጥንቸል ጋ ሄዶ ‹‹አትክልት ስጪኝ›› አላት፡፡

3

ጥንቸልም ‹‹እሺ፣ ወጡን አማስልልኝና›› አለችው፡፡ አናንሲ ግን ስራ አይወድም ነበር፡፡

4

አናንሲ ‹‹እስኪ ቆየት ብዬ እመጣለሁ›› አላት፡፡

5

አናንሲ በእግሮቹ ዙሪያና በጥንቸሏ ድስት ዙሪያ ድር አደራባት፡፡

6

‹‹ምግቡ ሲበስል ይህን ድር ሳቢው›› አላት፡፡

7

‹‹እናንተ ዝንጀሮዎች፣ እስኪ ምግብ ስጡኝ›› ሲላቸው ሸረሪቱ እነሱም መልሰው ‹‹መክተፉን ከረዳኸን እሺ›› ሲሉ መለሱለት፡፡

8

‹‹መጣሁ›› አለና አናንሲ ብዙ ድር አደራባቸው፡፡

9

‹‹አንቺ አሳማ ድንች ታበይኛለሽ?›› ‹‹ማዘጋጀቱን ካገዝከኝ ችግር የለም፡፡››

10

‹‹መጣሁ›› አለና አናንሲ ብዙ ድር አደራባት፡፡

11

እያንዳንዷ የአናንሲ እግር ከድስት ጋር ተሳሳረች ማለት ነው፡፡

12

አናንሲ ሁለተኛውን እግሩን የሆነ ነገር ሲስበው ተሰማው፡፡ ሦስተኛውንም…

13

ስምንቱም እግሮቹ እየተሳቡ ነው፡፡ ‹‹እንዴ በቃ አትሳቡኝ!›› አለ አናንሲ፡፡

14

አናንሲን ማንም አልሰማውም፡፡ የሸረሪት ድሩ አንድ ባንድ ተበጣጠሰ፡፡

15

የአናንሲ እግሮች ተሳሳቡ፡፡ በዚህም ምክንያት ሁሉም ሸረሪቶች እግሮቻቸው ረዘሙ፡፡

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሰነፉ አናንሲ
Author - Ghanaian folktale
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Wiehan de Jager
Language - Amharic
Level - First words