ጅብ፣ ጥንቸልና ሳፋዎቻቸው
Charles Katiwa Kiema

ጅብና ጥንቸል ጓደኛሞች ነበሩ፡፡

1

ጥንቸል አህያና ትንሽዬ ቀይ ሳፋ ነበሯት፡፡

2

ጥንቸል ትልቅ ሳፋ ሲያስፈልጋት የጅብን ሰማያዊ ሳፋ ትዋሳለች፡፡

3

ጅብ ልብሶቹን በሳፋው ለማጠብ ፈለገ፡፡

4

ጅብ ጥንቸል ጋ ሄዶ ‹‹ሳፋዬን ፈልጌው ነበር›› አላት፡፡

5

‹‹ሳፋህ ልጅ ነበራት›› ብላ ጥንቸል ሁለቱንም ሳፋዎች ሰጠችው፡፡

6

በሌላ ቀን ጥንቸል የጅብን ሳፋ እንደገና ተዋሰች፡፡

7

ጅብ ሳፋውን ሊወስድ ሲሄድ ጥንቸል መጥፎ ወሬ ነገረችው፡፡

8

‹‹ሳፋህ ሞተ›› አለችው ጥንቸል፡፡ ጅብ ይህን ሊያምን አልቻለም፡፡

9

ጅብ ትልልቆቹን እንስሳት ፍረዱኝ ብሎ ጠራ፡፡

10

‹‹ሕይወት ያላቸውና የሚወልዱ ነገሮች መሞታቸውም አይቀርም›› አለች ጥንቸል፡፡

11

እንስሳቱ ከጥንቸል ጋር ተስማሙ፡፡ የጅብንም ሳፋ ጥንቸል ወሰደችበት፡፡

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጅብ፣ ጥንቸልና ሳፋዎቻቸው
Author - Charles Katiwa Kiema
Translation - Mezemir Girma
Illustration -
Language - Amharic
Level - First words