እንቁራሪትና እባብ
John Emongot
Rob Owen

እንቁራሪትና እባብ ጓደኛሞች ናቸው፡፡

1

እንቁራሪት ‹‹ና፣ እናቴን ጎብኝልኝ›› አለችው ለእባቡ፡፡

2

‹‹አመሰግናለሁ›› አለ እባቡ፡፡ ‹‹ግን ቤቶቻችንን ማን ይጠብቅልናል?››

3

‹‹ቤቶቻችሁን እኔ አይላችኋለሁ›› አለች ዝንጀሮ፡፡

4

እንቁራሪት ነጫጭ ጉንዳኖችን በከረጢት ለእናቷ ያዘችላት፡፡

5

እንቁራሪትና እባብ በጠዋት መንገዳቸውን ጀመሩ፡፡ ወደ ደን ውስጥም ገቡ፡፡

6

የአይጠመጎጥ መንጋ አገኙ፡፡ እባብ ፈራ፡፡

7

እንቁራሪት ጓደኛዋን አዳነችው፡፡

8

እናቷ ቤት ሲደርሱ እርቧቸው ነበር፡፡

9

እጃቸውን ታጥበው ለመብላት ተዘጋጁ፡፡

10

‹‹እባብ፣ እባክህ ተቀመጥ›› አለችው እንቁራሪት፡፡

11

እባብ ለመቀመጥ ሞከረ፡፡ ግን እንቁራት ስላልሆነ አልቻለም፡፡

12

‹‹እኔ እንደ እንቁራት መቀመጥ አልችልበትም›› አለ እባቡ፡፡

13

እንቁራት አልሰማችውም፡፡

14

‹‹ልትረጂኝ ስላልቻልሽ ወደ ቤቴ እሄዳለሁ፡፡››

15

እባብ ተበሳጨ፡፡ ‹‹አይ፣ እንቁራት ጓደኛዬ መስሎኝ ነበር፡፡››

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
እንቁራሪትና እባብ
Author - John Emongot
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Rob Owen
Language - Amharic
Level - First words