ተወዳጇ ልጅ
Ritah Katetemera
Brian Wambi

ይቺ ናታቦ ናት፡፡ ስድስት ወንድሞች አሏት፡፡

1

ወላጆቿ አንድ ገንቦ ሰጧት፡፡ ያችን ገንቦም ትወዳታለች፡፡

2

አንድ ቀን ወንድሞቿ ገንቦን ሰበሩባት፡፡

3

ናታቦ ገንቦዋን ልታገኛት ስላልቻለች ማልቀስ ጀመረች፡፡

4

ናታቦ ሮጣ ጠፋችና አንድ ትልቅ ዛፍ ላይ ወጣች፡፡

5

ቤተሰቦቿ አገኟት፡፡ ‹‹እባክሽ ውረጂ›› በማለትም ለመኗት፡፡

6

ወንድሞቿ ‹‹እባክሽ ውረጂ›› በማለት ዘመሩ፡፡

7

ናታቦ በመዝሙራቸው አፌዘችባቸው፡፡

8

ከዚያ የናታቦ ጓደኛ መጣችና ‹‹እባክሽን ውረጂ››እያለች ዘመረችላት፡፡

9

የናታቦ ጓደኛ ከዛፉ ላይ እስክትወርድ ድረስ ዘመረች፡፡

10

ጓደኛሞቹ ወደ ቤት ሄዱ፡፡

11

ሁሉም ሰዎች ናታቦ ወደ ቤት በመመለሷ ተደስተው አዲስ ገምቦ ሰጧት፡፡

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ተወዳጇ ልጅ
Author - Ritah Katetemera, Mulongo Bukheye
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Brian Wambi
Language - Amharic
Level - First words