አካል ጉዳተኝነት ከምንም አያግድም!
Agnes Mabururu
Wiehan de Jager

ይህች ዓለም ትባላለች፡፡ አስተማሪዬ ናት፡፡

1

ዓለም በክራንች ለመራመድ ቻለች፡፡

2

ይህ ተዘራ ይባላል፡፡ በጣም የምወደው የሬድዮ የዘፈን ምርጫ አዘጋጅ ነው፡፡

3

ተዘራ ዓይኑ ማየት አይችልም፡፡

4

ይህች ዘርፌ ትባላለች፡፡ ጎረቤቴ ነች፤ ሥራዋም ግብርና ነው፡፡

5

ዘርፌ መናገር አትችልም፡፡ ነገርግን በምልክት ቋንቋ ትግባባለች፡፡

6

ይህ ፈጠነ ይባላል፡፡ በትምህርት ቤት ጥሩ የእግር ኳስ ተጫዋች ነው፡፡

7

ፈጠነ እጆች የሉትም፡፡ ግን ለቡድናችን ብዙ ግቦችን ያስቆጥራል፡፡

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አካል ጉዳተኝነት ከምንም አያግድም!
Author - Agnes Mabururu
Translation - ተስፋዬ ታጀበ, መዘምር ግርማ
Illustration - Wiehan de Jager
Language - Amharic
Level - First sentences