አባት እና ልጅ
Frista Nattabira
Wiehan de Jager

አበበ የሚባል አንድ ሰው ነበር፡፡

1

አበበ ከበደ የሚባል ልጅም አለው፡፡

2

አንድ ቀን ልጁን ‹‹ሽርሽር እንሂድ›› አለው፡፡

3

በመንገዱ ላይ ሲያልፉ የሚያምር ቦርሳ አገኙ፡፡

4

አበበ ደስ ስላለው ለልጁ ‹‹አንሳውና ወደ ቤት እንውሰደው›› አለው፡፡

5

ልጁም በአባቱ ምክር ተስማምቶ የታዘዘውን አደረገ፡፡ ከበደ ሻንጣውን ተሸክሞ ወደ ቤት ወሰደው፡፡

6

መንገድ ላይም ከቦርሳው ውስጥ እባብ መሰስ ብሎ ወጣ፡፡ በከበደ እግርም ላይ አረፈ፡፡

7

አባትና ልጅ በጣም ፈሩ! ከበደ ቦርሳውን ጣለው፡፡ በጣም በፍጥነትም እየሮጡ ጠፉ፡፡

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አባት እና ልጅ
Author - Frista Nattabira
Translation - የፈተ, አበበ
Illustration - Wiehan de Jager
Language - Amharic
Level - First paragraphs