ሃብታሟ ልጅ
Salaama Wanale
Mango Tree

ከዕለታት አንድ ቀን አስማረችና አበበች የተባሉ ሁለት እህትማማቾች ይኖሩ ነበር፡፡ ወላጆቻቸው ሞተዋል። የሚኖሩትም የተራቆተ መሬት ላይ ነበር። ዝናብም አይዘንብም፡፡ የሚበላ እህልም አልነበራቸውም። እነዚህ ሁለት እህትማማቾች የሚኖሩበት አካባቢ እህል የማይበቅልበት ስለነበረ የአካባቢው ሰዎች ምግብ ፍለጋ ሩቅ ቦታ ነበር የሚጓዙት፡፡

1

አስማረች ትሁት፣ ዝምተኛ፣ እና ሰው አክባሪ ነበረች። እህቷ አበበች ደግሞ ኩራተኛና የሰው ምክር የማትሰማ ልጅ ነበረች፡፡ ስለሌሎች ሰዎች ምንም አታስብም ነበር።

2

አንድ ቀን ጠዋት እህትማማቾቹ ከእንቅልፋቸው ሲነሱ ከቤታቸው ውስጥ ምግብ የሚባል ነገር የለም ነበር። ከዚያም ምግብ ፍለጋ ወደተለያየ ቦታ ሄዱ፡፡

3

እትዬ ነፃነት የሚባሉ አዛውንት ሴትዮም ነበሩ፡፡ በጣም ጥሩ ሰው ነበሩ። እኝህ አዛውንት ሴትዮ የለምጥ በሽተኛ ስለነበሩ ሰውነታቸው በሙሉ ቁስል በቁስል ሆኖ ነበር።

4

አበበች በመንገድ ላይ እየተጓዘች ሳለች እትዬ ነጻነት አገኟትና''እንደምን አደርሽ ልጄ? ከየት ነው የምትመጪው? ወዴትስ እየሄድሽ ነው?'' አሏት።

5

አበበች ወዴት እየሄደች እንደሆነ ለአዛውንቷ ነገረቻቸው። አዛውንቷ ሴትዮ ደግሞ  ''እሺ ልጄ፣ አዝለሽ ቤቴ ካደረስሽኝ የፈለግሽንውን ነገር እሰጥሻለሁ'' አሏት። አበበች ግን ለሴትዮዋ ጥሩ አልመለሰችም።

6

''ይህን ቁስልዎን ከምነካ ብሞት ይሻለኛል'' አለቻቸው። አዛውንቷ ሴትዮም ''ሂጂ ይቅናሽ'' አሏት።.

7

አበበች ጉዞዋን ቀጠለች፡፡ በጣም ስላራባትና ስለደከመች ትንሽ አረፍ ለማለት ትልቅ ዛፍ ስር ቁጭ አለች። የተቀመጠችበት ቦታ በጊንጦች፣ በእባቦችና እንሽላሊቶች ተሞልቶ ነበርና ተረባርበው ነደፏት። ከዛም አውሬ በላት፡፡

8

አሁን ደግሞ እኚሁ አዛውንት ሴትዮ ከአስማረች ጋር መንገድ ላይ ተገኛኙና ''እንደምን አደርሽ ልጄ? ወዴት እየሄድሽ ነው?'' አሏት። አስማረችም ወዴት እየሄደች እንደሆነ ነገረቻቸው። እትዬ ነጻነትን ስታይ በጣም ደስ ብሏት ነበር፤ ምክንያቱም መንገድ ከጀመረች ያገኘቻቸው የመጀመሪያዋ ሰው ስለሆኑ። ከዛም አዛውንቷ ''አዝለሽ ቤቴ ካደረስሽኝ የፈለግሽውን ነገር እሰጥሻለሁ'' አሏት፡፡

9

አስማረች ትሁት ልጅ ስለነበረች አዝላ ቤታቸው ድረስ ወሰደቻቸው፡፡ ''በዪ ለጄ ማንም ሊያደርገው ያልቻለ ነገር ነው ያደረግሽው'' አሏት። ''እናም ይህን ምርኩዝ ይዘሽ ወደቤትሽ ሂጂ'' አሏት። አስማረችም ምርኩዙን ይዛ ወደ ቤቷ ተመለሰች።

10

አስማረችም እቤት ስትደርስ ያልጠበቀችው ነገር ገጠማት፤ ቤታቸው ታድሶ እና በምግብ ተሞልቶ አገኘችው፡፡ ከዚያም የመንደሩ ሃብታም ሴት ሆነች፡፡

11

ነገር ግን በእህቷ ሞት አዘነች። ''ምክር ያልሰማ ሰው መጨረሻው ዝሆን አፍ ውስጥ ነው!'' አለች።

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሃብታሟ ልጅ
Author - Salaama Wanale
Translation - ፋሲካ ምንዳ, መዘምር ግርማ
Illustration - Mango Tree
Language - Amharic
Level - First paragraphs