አባቱን የታደገው ጥላሁን
Kanyiva Sandi
Benjamin Mitchley

በዱሮ ዘመን ከአባቱ ጋር የሚኖር ጥላሁን የተባለ ልጅ ነበር። የጥላሁን አባት አቶ አበበ ይባላሉ፡፡

1

እናም አቶ አበበ ሁሌ ወደ ቤታቸው የሚመጡት ሲጠጡ ያመሹና ነበር።

2

ሁሌ ሰክረው በመጡ ቁጥር መንደሩን በጩኸት ያናውጡት ነበር፡፡ ''ሰፈር፥ሰፈር! ኡ ኡ ኡ! እርዱኝ! ጅብ ሊበላኝ ነው!'' እያሉ ይጮሀሉ፡

3

የአቶ አበበን ጩኸት የሰሙ የሰፈሩ ሰዎች አቶ አበበን ለመርዳት ጦርና ገጀራ ይዘው ይወጣሉ። ነገር ግን ወጥተው ሲያዩት ምንም ጅብ የሚባል ነገር የለም። ከዚያም ሰፈርተኛው ሁሉ ''ምን አደረግነው ይህ ሰው? እንቅልፍ አሳጣን እኮ'' እያሉ ወደየቤቶቻቸው ይመለሳሉ፡፡

4

የጥላሁን አባት መስከራቸውንና ለእርዳታ መጮሃቸውን ቀጠሉ። ሰፈርተኛውም አቶ አበበን ለመርዳት ጦርና ገጀራ ይዞ ይወጣል፡፡  ነገር ግን ሁልጊዜም ተመሳሳይ ታሪክ ነው፤ እያሾፉባቸው ነበር።

5

ሁልጊዜም አባትዬው አምሽተው በመጡ ቁጥር ጥላሁን በጩኸታቸው ይነቃል። ጥላሁን የአባቱን ድምጽ በደንብ ያውቃል። አቶ አበበ በጨለማ ውስጥ ሲራመዱ ኮቴያቸው በሩ ጋር እስኪደርሱ ይሰማል።

6

አንድ ምሽት አቶ አበበ ሰክረው እየጮሁ ሲመጡ መንገድ ላይ ጅብ አገኛቸው። አቶ አበበም ''ኡ ኡ! እርዱኝ! ጅብ ሊበላኝ ነው'' እያሉ መጮህ ጀመሩ። አቶ አበበም ሲጮሁ፥ ጅቡ አጠቃቸው።

7

የሰፈሩ ሰዎች ደግሞ ''ምን አደረግነው እንቅልፍ የሚያሳጣን ይህ ሰካራም!'' እያሉ ሳይመጡላቸው ቀሩ፡፡

8

ነገር ግን አቶ አበበ ጩኸታቸውን አላቋረጡም ''ኡ ኡ እርዱኝ'' ማለታቸውን ቀጠሉ፡፡ ከዚያም ልጃቸው ጥላሁን ተጠራጠረና ማዳመጥ ጀመረ፡፡ ነገር ግን የአባቱን ኮቴ ለመስማት አልቻለም፡፡

9

''አባቴ አደጋ ላይ ሳይሆን አይቀርም'' አለ ጥላሁን። ''አሁንስ እያሾፈ አይደለም፡፡''.

10

ጥላሁን ከአልጋው ዘሎ ወረደ። ምድጃ ውስጥ ተማግዶ የነበረ ፍልጥ ይዞ በፍጥነት ከጎጆው ወጣ።

11

''አባቴ፥ አባቴ!'' አለ። በጨረቃ ብርሃን፥ አባቱ ከጅቡ ጋ እየታገሉ አያቸው፡፡ ከዛም በእጁ በያዘው ፍልጥ ጅቡን አባሮ አባቱን ታደገ፡፡ ጅቡም ፍልጡን ባየ ጊዜ ሮጦ አመለጠ።.

12

ከዛን ቀን ጀምሮ አቶ አበበ መጠጥ መጠጣት ተዉ። ለተማሪዎች ተረትና ታሪክ በማስተማር ጊዜያቸውን ማሳለፍ ጀመሩ፡፡

13
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አባቱን የታደገው ጥላሁን
Author - Kanyiva Sandi
Translation - ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ, መዘምር ግርማ
Illustration - Benjamin Mitchley
Language - Amharic
Level - Longer paragraphs