ታማኝነት የጎደለው ጓደኛ
Garba Yahaya

በአንዲት ደመቅ ባለች የአፍሪካ መንደር ውስጥ፣ ንዳቤ የተባለ ዝንጀሮ እና ንዳኮሮ የተባለች ሚርካት (ትናንሽ ፍልፈል የመሰለች እንስሳ) የልብ ጓደኛሞች ነበሩ።

አብረው ይጫወታሉ፣ አብረው ይበላሉ፤ "ሁልጊዜ ሁሉንም ነገር ሁሉ እኩል እንካፈላለን!" ብለውም ቃል ተገባቡ።

1

አንድ ቀን፣ አንድ የማንጎ ዛፍ አገኙ። ንዳቤ "ፍሬውን በታማኝነት እኩል እንከፋፈል!" አለ።

ንዳኮሮ ግን በልቡ "እኔ ይበልጥ ይገባኛል!" ብሎ አሰበ። ከዚያም የተወሰኑ ማንጎዎችን በጉድጓዱ ውስጥ ደበቀ።

2

ንዳቤ "የእኔ ማንጎዎች ለምን አነሱ?" ብሎ ጠየቀ።

ንዳኮሮ ግን "ወፎች ሰርቀውት ነው!" በማለት ዋሸ። ንዳቤ ግራ ተጋባ፣ ሆኖም ጓደኛውን አምኖ ዝም አለ።

3

ቆየት ብሎም፣ ንዳኮሮ የአንድ ንብ ቀፎ አገኘ። ንዳቤም "ማሩን እንካፈላል!" ብሎ ጮኸ።

ንዳኮሮ ግን ተጣባቂ እጆቹን እየላሰ፣ "ንቦቹ ምንም ማር አላስቀሩም!" በማለት ዋሸ።

4

ንዳቤ ጥርጣሬ አደረበት ወጥመድ ዘረጋ እና "ከንቦቹ የተሰጠ ስጦታ!" ብሎ ተናገረ።

ንዳኮሮ በሌሊት በዝግታ እያደባ መጣ እና ንዳቤ ያዘጋጀው ጉድጓድ ውስጥ ዘጭ ብሎ ወደቀ!

5

ንዳቤ "ለምን ዋሸኸኝ?" ብሎ ጠየቀው።

ንዳኮሮ እያለቀሰ "ለራሴ ብዙ እንዲኖረኝ ፈልጌ ነው!" ብሎ መለሰ።

ንዳቤ በሀዘን ትንፋሹን እየሳበ፣ "ታማኝ አለመሆን መተማመንን ይሰብራል" አለው።

6

ንዳኮሮ የሰረቀውን ሁሉ መለሰ። "ይቅር በለኝ" ሲል ለመነ።

የመንደሩ ነዋሪዎችም "ለመሆኑ ይሄ ልጅ ይለወጥ ይሆን?" እያሉ በሹክሹክታ ተነጋገሩ።

7

ንዳኮሮ እንደገና ታማኝነቱን ለማሳየትና የጠፋውን መተማመን ለመገንባት ጠንክሮ ሰራ። ንዳቤም ፈገግ ብሎ፣ "እውነተኛ ጓደኝነት ታማኝነት ያስፈልገዋል" አለው።

ከዚያን ቀን ጀምሮ ዳግመኛ ምንም ነገር ላለመደባበቅ ወይም ላለመዋሸት ቃል ገቡ።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ታማኝነት የጎደለው ጓደኛ
Author - Garba Yahaya
Translation - Tesfamichael Hailu, Yeabsra Asfaw
Illustration -
Language - Amharic
Level - First paragraphs