ጊዜ
Mimi Werna

ጊዜ ልክ እንደ ስጦታ እሽግ ነው።

1

በዚህ ትልቅ የጊዜ ስጦታ ውስጥ፣ ደግሞ ሌሎች ብዙ ትናንሽ ስጦታዎችን ታገኛለህ።

2

አንዱ የእሽግ ስጦታ አንድ ሙሉ ቀን ማለት ነው።

አንድ ቀን ደግሞ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ (86,400) ሰከንዶች አሉት።

3

ይህን የጊዜ ስጦታ መክፈትና በአግባቡ መጠቀም ይኖርብሃል።

አዳዲስ ነገሮችንም ተማር።

4

ብላ።
ተጫወት።
እረፍት አድርግ።
አልም።
አስብ።

5

ዛፍ ተክሉ፣ ጫካው ይበቅላል።

ችግርን ይፍቱ።

6

ገንዘብህ እያደገ (እየጨመረ) ሲሄድ፣

ጥቂቱን አስቀምጥ (ቆጥብ)፣
ጥቂቱን ተጠቀምበት (አውጣው)
ጥቂቱን ደግሞ ለሌሎች አካፍል።

7

ካልተሳካልህ እንደገና ጀምር።

ጊዜ ስጦታዎችን በቀናት ጠቅልሎ ያቀርባል።

8

ሰኞ እና ማክሰኞ።
ረቡዕ እና ሐሙስ።
አርብ እና ቅዳሜ፣ እሑድ እንኳን።

9

እነዚህ ልዩ ጓደኞች ናቸው።

በጓደኝነታቸው ተደሰት።

10

ሰዓቱ 'ቲክ ቶክ' እያለ ሲቆጥር፣ የእኔን ቃላት አስታውስ።

11

ጊዜ የተለየ (አስገራሚ) እሽግ ነው፤ እጅግ ልዩ የሆነ ስጦታ።

በአግባቡ ተጠቀምበት።

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጊዜ
Author - Mimi Werna
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration - , Joe Werna
Language - Amharic
Level - First sentences