ደጉ ሳምራዊ
Gloria Owusu Agyeiwaa

ደዴ እና አዳኩ በጣም የቅርብ ጓደኛሞች ነበሩ።

ዶዶዋ በሚባል ከተማ ውስጥም አብረው ይኖሩ ነበር።

1

አንድ ቀን፣ ማንጎ ለመልቀም ወደ ዶዶዋ ደን ለመሄድ ወሰኑ።

ወደ ደኑ ውስጥ ዘልቀው (በጣም ርቀው) ገቡ።

2

ብዙ ማንጎዎችን ለቀሙ፤ ቅርጫቶቻቸውንም ሙሉ በሙሉ ሞሏቸው።

3

ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ሳለ፣ መንገዱ ጠፋባቸው።

4

መጨለም ስለጀመረ በጣም ፈሩ።

እባካችሁ እርዱን! እያሉ መጮህ ጀመሩ።

5

ድንገት አንድ ሰው ብቅ አለና፦ "በዚህ ባልተለመደ (በመሸ) ሰዓት በጫካ ውስጥ ምን ታደርጋላችሁ?" ሲል ጠየቃቸው።

እነሱም ማንጎ ለቅመው ሲመለሱ ወደ ቤታቸው የሚወስደው መንገድ እንደጠፋባቸው ነገሩት።

6

ሰውየውም እስከ ቤታቸው ድረስ አምጥቶ ለወላጆቻቸው አስረከባቸው።

7

ወላጆቻቸው ልጆቻቸውን በማየታቸው በጣም ተደሰቱ፤ ሰውየውንም አመሰገኑት።

ሰውየውም 'ደግ ሳምራዊ' ነበረ።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ደጉ ሳምራዊ
Author - Gloria Owusu Agyeiwaa
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration -
Language - Amharic
Level - First paragraphs