

በእርሻው ላይ በጣም ሞቃታማና ፀሐያማ የሆነ የቅዳሜ ጠዋት ነበር። ማያ፣ ዱክሲ እና ዱቢ እማማ ኬን በአትክልት ስፍራቸው ውስጥ እያገዟቸው ነው። ልጆቹ ጠዋቱን ሙሉ በትጋት ሲሰሩ ዋሉ።
መጀመሪያ አፈር ውስጥ ማዳበሪያ ቀላቀሉ፤ ከዚያም አረሙን እየነቀሉ አትክልቶቹን ውሃ አጠጡ። በመጨረሻም የደረሱትን ሰብሎች ሰበሰቡ።
ዛሬ እያንዳንዳቸው ልጆች አዲስ የተቀጠፈ እንጆሪ፣ ቆስጣ እና ካሮት ወደ ቤታቸው ይዘው ይሄዳሉ።
እማማ ኬ ለሚረዷቸው ልጆች ሁልጊዜም ጣፋጭ ሽልማት ይሰጣቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ሽልማቱ ኬክ፣ ቸኮሌት፣ ወይም ደግሞ እባብ የሚመስሉ ረዣዥም ከረሜላዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ሌላ ጊዜ ደግሞ ፖም፣ ፒር ወይም ብርቱካን ይሰጧቸዋል።
እማማ ኬ ግን አንዲት የማይለወጥ ሕግ አላቸው። እሷም, "እኩል አካፍሉ!" የምትል ነች። ልጆቹ ሽልማቱን እያንዳንዳቸው ተመሳሳይ መጠን እንዲደርሳቸው አድርገው በፍትሐዊነት መከፋፈል እንዳለባቸው ያውቃሉ።
ዛሬ እማማ ኬ ከራሳቸው የአትክልት ስፍራ በተቀጠፈ እንጆሪ የተሰራና በሮዝ ቀለም ያሸበረቀ ክብ ኬክ ጋገሩ። ልጆቹ ሽልማታቸውን ለመቀበል ሳሩ ላይ ተቀምጠው እየጠበቁ ነው።
እማማ ኬ ፈገግ እያሉ, "እንካችሁ!" አሏቸው። "ግን ሕጉን እንዳትረሱ፤ እያንዳንዱ ሰው እኩል ማግኘት አለበት። በፍትሐዊነት ተካፈሉ! እንዳትጣሉ!" በማለት አሳሰቧቸው።
ኬኩን የማከፋፈል የመጀመሪያው ተራ የማያ ሆነ። ማያ ቢላዋውን አንስታ በኬኩ የላይኛው ክፍል (አይሲንጉ) ላይ የመቁረሻ መስመሮችን ማሰመር ጀመረች። ሌሎቹ ልጆች በትኩረት ይመለከቷታል። ገና ኬኩን አልቆረሰችውም፤ በመጀመሪያ ሁሉም ልጆች አከፋፈሏ ፍትሐዊ መሆኑን መስማማት አለባቸው።
ማያም, "እንደዚህ አድርጌ ሁለት ቦታ የምቆርሰው ይመስለኛል። አሁን ለሦስታችንም እኩል የሆነ ሦስት ቁራጭ ይኖረናል!" እያለች አሳየቻቸው።
"በፍጹም አይሆንም!" አለ ዱክሲ። "መሃል ላይ ያለው ቁራጭ በጣም ትልቅ ነው!"
ዱቢም ጭንቅላቱን በመነቅነቅ አልተስማማም። ማያ እየሳቀች ትከሻዋን ሰበከችና (አልተሳካልኝም በሚል ስሜት)፣ አሁን ደግሞ ዱክሲ እንዲሞክር ተራውን ሰጠችው።
"አምጪው! ቢላዋውን ለእኔ ስጪኝ፣ እኔ አደርገዋለሁ። በጣም ቀላል ነው!" እያለች ዱክሲ በራስ መተማመን በታየበት ድምፅ ተቀበለች።
መጀመሪያ፣ ማያ በአይሲንጉ ላይ ያሰመረችውን ምልክት በእጇ አጠፋችና ጣቶቿን ላሰች።
ከዚያም ዱክሲ አንዱን መስመር አግድም፣ ሌላኛውን ደግሞ ቁልቁል አሰመረች። "ተመልከቱ! እነዚህ የእኔ ሦስት ቁራጮች ናቸው!" አለች።
"ይህ በፍጹም ፍትሐዊ አይደለም!" በማለት ማያ እና ዱቢ በአንድ ላይ ጮኹ።
"እኩል አካፍሉ! ቁራጮቹ መጠናቸውም ሆነ ቅርጻቸው ተመሳሳይ መሆን አለበት," ሲል ዱቢ አከለበት።
ዱክሲም በፌዝ ፈገግ እያለች, "ለምን አንተ አትሞክረውም ዱቢ? አንተም ልታደርገው እንደማትችል እርግጠኛ ነኝ!" አለችው።
ዱቢ በጥልቀት እያሰበ, "ኬኩ ካሬ ወይም አራት ማዕዘን ቢሆን ኖሮ፣ ለመከፋፈል በጣም ቀላል በሆነ ነበር!" አለ።
ማያም በበኩሏ, "ወይም ደግሞ፣ ይህንን ክብ ኬክ የምንካፈለው አራት ብንሆን ኖሮ እሱም ቀላል ይሆን ነበር" ስትል አሳቧን ገለጸች።
ከዚያም ድንገት በዱቢ አእምሮ ውስጥ አንድ ምስል መጣ። የአባቱን ትልቅ ቀይ መኪና (ትራክ) ፊት ለፊት ላይ ያለውን የሚያብረቀርቅ የብር ምልክት (ባጅ) በዓይነ ሕሊናው ተመለከተ።
እሁድ እሁድ አባቱን መኪናውን ሲያጥብ ይረዳዋል፤ ያንን የሚያብረቀርቅ ምልክትም ይወለውላል። "አገኘሁት! አገኘሁት! እንዴት መደረግ እንዳለበት አወቁ!" እያለ ዱቢ በደስታ ጮኸ።
መጀመሪያ፣ ዱክሲ በአይሲንጉ ላይ ያሰመረችውን መስመር በቢላዋው አስተካክሎ አጠፋው። ከዚያም በኬኩ ላይ ሦስት መስመሮችን አሰመረ።
ልክ እንደ አባቱ መኪና ምልክት፣ ኬኩ አሁን በሦስት እኩል ክፍሎች የተከፈለ ይመስላል።
ዱክሲ በለሰለሰ ድምፅ, "ዱቢ፣ ሁልጊዜም በአዳዲስ ነገሮች ታስገርመናለህ!" አለችው። ማያም በበኩሏ "እንዴት ልታውቀው ቻልክ?" ስትል በግርምት ጠየቀችው።
ዱቢ ለራሱ ፈገግ አለ። ለጊዜው ምስጢሩን በሆዱ ያዘው። ቆየት ብሎ ግን ለአባቱ ይነግረዋል።
ልክ በዚያ ቅጽበት እማማ ኬ ከቤታቸው ወጡ። በእጃቸውም በብርጭቆ የተሞላ የእንጆሪ ጭማቂ የያዘ ትሪ ይዘዋል። ማያም "እማማ ኬ ተመልከቱ! ዱቢ ኬኩን ለሦስታችንም እኩል የምንከፍልበትን መንገድ አገኘ!" በማለት ነገረቻቸው።
እማማ ኬም "ጎበዝ ዱቢ! ሦስት እኩል ቁራጮች! በፍትሐዊነት ተካፍላችኋል፤ በሁላችሁም ኩራት ይሰማኛል። አሁን ኬኩን ቁረሱና ጭማቂውን ጠጡ። ወደ ቤት የምትሄዱበት ሰዓት ደርሷል" አሏቸው።
ማያ የዱቢን መስመሮች በመከተል ኬኩን በሦስት እኩል ቁራጮች ቆረሰችው።
ልጆቹ ለጨዋታ ያህል፣ ቁራጮቹ በእርግጥ ተመሳሳይ መጠን መሆናቸውን ለማረጋገጥ አንዱን በሌላው ላይ ደራረቧቸው። በትክክልም እኩል ናቸው! ከዚያም ኬኩን ወደ ቤታቸው ለመውሰድ በፓስታ አሸጉት።
የዱቢ አባት ልጆቹን ለመውሰድ መጣ፤ ዱቢም እሱን ለመቀበል እየሮጠ ሄደ።
በትራክ መኪናው ላይ ያለው ምልክት (ባጅ) ያንንም በጣም አስቸጋሪ የሆነ የሒሳብ እንቆቅልሽ ለመፍታት እንዴት እንደረዳው ለአባቱ ለመንገር በጣም ጓጉቷል!
ልክ መኪናዉ ዉስጥ አንደገባ ዱቢ የዛሬዉን ዉሎ ፡ ማማ ኬ ጋ የገጠመዉን ችግር ፡ አንዴት የ መኪናቸዉን ባጅ ተጠቅሞ አንደፈታዉ ለ አባቱ ነግሮት አየተሳሳቁ በድል ኣድራጊነት ስሜት ተሞልቶ ስለማካፈል ያደረገዉን ነገር ለአባቱ በመንገሩ ተደስቶ ወደቤታቸዉ ሄዱ።

