ሲንዲ እና ማኒኩዊንስ
Mpho Sanny Sabasaba

ሲንዲ ስለ ዓለም የማወቅ ጉጉት ያላት ቆንጆ ወጣት ልጅ ነበረች።

1

ከእናቷ ጋር በልብስ መደብር ውስጥ ለመስራት መሄድ ያስደስታት ነበር።

2

ሲንዲ ወደ ልብስ መደብሩ በሄደች ቁጥር፣ ማኒኩዌንሶቹን (አሻንጉሊቶቹን) መንካት ትወድ ነበር።

3

ለእናቷም የልዩ ልዩ ጥያቄዎችን ታዥጎደጉድላት ነበር።

"እማዬ፣ ማኒኩዌንሶች ማውራት ይችላሉ?"

"እጆቼ ሲነኳቸው ሊሰማቸው ይችላል?"

"ሊያዩኝ ይችላሉ?"

4

እናቷም "ሲንዲ፣ ማኒኩዌንሶቹን አትንኪ" ብላ ትመልስላት ነበር።

አንድ ቀን ምሽት፣ የሲንዲ እናት ሱቁን ዘግታ ከወጣች በኋላ፣ ማኒኩዌንሶቹ ተሰባሰቡ።

5

ሲንዲ ምን ያህል ደስተኛ እን እንዳላደረገቻቸው (እንዳሳዘነቻቸው) ያወሩ ጀመር።

"ክትክት! ክትክት! ክትክት!" አለ ወንዱ ማኒኩዌን። በመቀጠልም "የእግር ጥፍሮችሽን እቀባቸዋለሁ" ብሎ ንግግሩን ቀጠለ።

6

"ኦህ፣ በፍጹም! እኛ ጥፍራችንን አንቀባም" አለች ሴቷ ማኒኩዌን።

ስለሆነም፣ ማኒኩዌንሶቹ በሲንዲ ላይ እንዴት አጸፋ መመለስ (ለመበቀል) እንደሚችሉ መንገድ ሲፈልጉ ሌሊቱን ሙሉ ሳይተኙ አደሩ።

7

በማግስቱ ሲንዲ በደስታና በንቃት እየፈነጠዘች፣ ከማኒኩዌንሶቹ ጋር ለመጫወት ዝግጁ ሆና ወደ መደብሩ መጣች።

ሁሉንም እየነካካች ተጫወተች። ነገር ግን ወንዱን ማኒኩዌን ለመንካት ስትሞክር፣ "ቡ!" (Boo!) በማለት ትልቅ ድንጋጤ ውስጥ ከተታት።

8

"እማዬ!" ብላ ጮኸች ሲንዲ። እናቷም ምን ሆና እንደሆነ ለማየት እየሮጠች መጣች።

ሲንዲ ማኒኩዌኑ እንዴት እንዳስደነገጣት ለእናቷ ነገረቻት። የሲንዲ እናት ግን "የኔ ሞኝ ሲንዲ" ብላ ሳቀች።

9

"የኔ ልጅ፣ ማኒኩዌንሶች ማውራት አይችሉም፤ ሊነኩሽም ሆነ ሊያዩሽም አይችሉም" አለች የሲንዲ እናት።

"ኦህ እናቴ፣ ለጥያቄዎቼ መልስ እንድትሰጪኝ ማኒኩዌንሶቹ ሊያስደነግጡኝ ይገባ ነበር ማለት ነው?" ብላ መለሰች ሲንዲ። እሷና እናቷም አብረው ሳቁ።

10
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሲንዲ እና ማኒኩዊንስ
Author - Mpho Sanny Sabasaba
Translation - Tesfamichael Hailu, Yeabsra Asfaw
Illustration -
Language - Amharic
Level - First paragraphs