አቢ እና ላይላ
Tony Lelliott

አቢ እና ላይላ በጆሃንስበርግ የሚኖሩ ሁለት ውሾች ናቸው።

ሁለቱም የሁለት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ናቸው።

1

በአትክልታቸው ውስጥ መጫወት ይወዳሉ።

2

አቢ እና ላይላ ወደ ፓርኩ መሄድ ይወዳሉ።

በፓርኩ ውስጥ በፍጥነት መሮጥ ይችላሉ።

3

በፓርኩ ውስጥ ባሉ ትናንሽ ጅረቶች ላይ መዝለል ይችላሉ።

4

አቢ እና ላይላም በኮረብቶች ላይ መሮጥ ይወዳሉ።

5

በኮረብቶች ላይ ከሌሎች ውሾች ጋር ይጫወታሉ።

6

ወደ ቤት ሲደርሱ፣ ሮጠው ከሄዱ በኋላ በጣም ደክሟቸዋል።

ሹሽ፣ አቢ እና ላይላ ተኝተዋል!

7
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አቢ እና ላይላ
Author - Tony Lelliott
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration -
Language - Amharic
Level - First sentences