

እናቲቱ ልብሶቿን በትንሽ ቦርሳ ውስጥ ከትታ እየጨረሰች ነበር።
በበሩ በኩል ወደ ውጭ ስትወጣ እቅፍ አደረገችኝና, "ለአሁኑ ደህና ሁኚ።"
ቀና ብዬ አየኋትና "ዉድ እናቴ ፥ ወዴት እየሄድሽ ነው?" ብዬ ጠየቅኳት።
ልከተላት ፈልጌ ማልቀስ ጀመርኩ ግን አባቴ እሽኮኮ ብሎ በትከሻው ላይ አስቀመጠኝ።
አባዬ "እናትሽ ልጅ ልትወልድ ወደ ሆስፒታል እየሄደች ነው።" አለኝ።
"ህፃን" የሚለውን ስሰማ ማልቀሴን ትቼ ተመለከትኩት።
"ሕፃኑን ከሆስፒታል ለምንድን ነው የምታመጣው?" ስል ጠየኩት።
አባዬ ትንሽ ወንበር ላይ አስቀመጠኝ እና "ልጁን ከሆስፒታል ለምን እንደምታመጣ እነግርሻለሁ" አለኝ።
ሲያብራራ በጥሞና አዳመጥኩት። ነገር ግን ልጅዋን ቤት ውስጥ ለምን እንደማትወልድ በደንብ አልገባኝም።
አባቴ ገለጻውን እንደጨረሰ፣ "ከሌላው ህፃን ጋር ስትመለስ አሁንም ትወደኛለች?" ስል ጠየኩት።
አባቴ ጠጋ ብሎኝ "ሁልጊዜ እንወድሻለን" አለኝ።
"እሷ ሆስፒታል እያለች ደብዳቤ ልጽፍላት እችላለሁ?" ስል አባቴን ጠየቅኩት።
በዚያ ምሽት ለእማዬ ደብዳቤ መጻፍ ጀመርኩ።
ከመልመጃ መጽሐፌ ላይ አንድ ወረቀት ቀደድኩ።
መጻፍ ጀመርኩ ...
እማዬ፣ እማዬ፣ አባዬ ሌላ ልጅ ልታመጣ ነው የሄደችው ብሎ ነግሮኛል።
እባክሽ ፈጥነሽ ወደ ቤት ተመለሺ።
ሴት ልጅ እንድታመጪ እፈልጋለሁ።
ስታድግ ከእሷ ጋር መጫወት እፈልጋለሁ።
ሁለት ልጅ ይዘሽ ነይ አንዱ የኔ እንዲሆን።
እዚህ ከቤታችን ውጭ እየጠበኩሽ ነው።
ደብዳቤዬን አባቴ ወስዶ ለእናቴ እንዲሰጥልኝ አጠፍኩት።
በማግስቱ ጠዋት ስነቃ ደብዳቤው በነበረበት አልነበረም።

