ሴቲማሞሌሎ እና ባለ ሦስት እግሩ ድስት
Pelonomi Itumeleng
Rob Owen

ሴቲማሞሌሎ በኩሩማን የሚኖር የ12 ዓመት ታዳጊ ነበር። እርሱም እጅግ ብልህና ተሰጥኦ ያለው ልጅ ነበር።

ከታደላቸው ልዩ ስጦታዎች አንዱ ከአፉ እሳት የመተንፈስ ችሎታው ነበር። ይህ ችሎታው የሚያስደንቅ ቢሆንም በዚያው ልክ አደገኛም ነበር።

1

አንድ ምሽት እሳቱ አጠገብ ተቀምጦ ሳለ፣ ከሚንቦገቦገው ነበልባል ውስጥ አምስት ጥላዎች ሲወጡ ተመለከተ። እነርሱም የእርሱ ዘመዶችና አያቶቹ ነበሩ። እነርሱም በአንድ ወቅት እንደ እርሱ ዓይነት ልዩ ስጦታ የነበራቸው ቢሆንም ካለፉ ግን ቆይተዋል።

እሳቱ እየጨመረና ይበልጥ እየደመቀ መጣ፤ ከዚያም ልክ እንደመጡት ሁሉ በድንገት ተሰወሩ።

2

ከጥቂት ቅጽበታት በኋላ፣ ደኑ በነበልባል ተዋጠ። ሰዎች ይሮጡ ነበር፣ ቤቶች ይቃጠሉ ጀመር፣ አየሩም በሁከትና በግርግር ተሞላ።

ዶሮዎች፣ ውሾችና ፍየሎች በፍርሃት ተበታተኑ። እሳቱም ሊቆም በማይችል ሁኔታ እየተፋፋመ ቀጠለ።

3

ሜዳ ፍየሎቹ (Springboks) ሳይቀሩ ወደ ላይ እየዘለሉ ወደ ጋሞሃና ኮረብታዎች ሸሹ።

እሳቱ በመንገዱ ያገኘውን ሁሉ አወደመ፤ ብዙም ሳይቆይ የማሩፒንግ መንደር ወደ አመድነት ተቀየረች።

4

ሴቲማሞሌሎ በባለ ሦስት እግሩ ድስት ስር እሳት በለኮሰ ቁጥር የሚሰማውን አንድ ነገር አስታወሰ። ድምፁም እንዲህ ይል ነበር፦ "የአንተ እሳት፣ የአንተ ቁጥጥር!"

እሳትን እንዴት መፍጠር እንደሚችል ተምሯል፣ ነገር ግን እንዴት መቆጣጠር እንዳለበት ግን አላወቀም ነበር። መንደሩን ለማዳን በቆራጥነት፣ ስጦታውን የሚገዛበትን መንገድ ፍለጋ ወደ ጋሞሃና ኮረብታዎች ሮጠ።

5

በኮረብታው ጫፍ ላይ ወንድሙ ሲጠብቀው አገኘው። ወንድሙም አንድ ልዩ የዛፍ ቅርፊት በመጠቀም እሳትን እንዴት ማጥፋት እንደሚቻል አሳየው።

ሴቲማሞሌሎ ስጦታውን ለመቆጣጠር በመቁረጥ፣ ቀን ከሌሊት ሳይሰለች ልምምድ አደረገ።

6

ጨለማው ሰፍኖ ከዋክብት በሰማይ ላይ በሚደሰቱበት ጊዜ፣ የመንደሩ ነዋሪዎች በኮረብታው አናት ላይ እሳት ሲንቦገቦግ ይታያቸው ነበር።

ከጥቂት ቅጽበታት በኋላ ግን፣ እሳቱ ጠፍቶ አካባቢው በጭለማና በዝምታ ይዋጣል። ሴቲማሞሌሎ ደጋግሞ ልምምዱን ቀጠለ።

7

በመጨረሻም የማሩፒንግ መንደር ተመልሳ ስትገነባ፣ ሴቲማሞሌሎ ያለውን ልዩ ስጦታ ለታዳጊ ሕፃናት ማሳየት ጀመረ።

ነገር ግን ከሁሉ በላይ ደግሞ፣ ያ ባለ ሦስት እግሩ ድስት በጆሮው ያንሾካሾከለትን ጥበብ አስተማራቸው፦ "የአንተ እሳት፣ የአንተ ቁጥጥር!" ነው።

ሴቲማሞሌሎ ከመንደሩ መጥፋት ተምሮ ታላቅ መሪ ሆነ። ለሕፃናቱ የሚያሳያቸው ጨዋታ ብቻ ሳይሆን፣ ስሜታችንን እና ድርጊታችንን እንዴት መቆጣጠር እንዳለብን ጭምር ነው። ዛሬም በማሩፒንግ መንደር "የለኮስከውን እሳት መቆጣጠር የአንተ ድርሻ ነው" የሚለው ጥበብ እንደ ትልቅ መመሪያ ይነገራል።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሴቲማሞሌሎ እና ባለ ሦስት እግሩ ድስት
Author - Pelonomi Itumeleng
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration - Rob Owen
Language - Amharic
Level - Read aloud