እኔ ብሆን ኖሮ
Kabubbu pilot site

እኔ የባንክ ሥራ አስኪያጅ ብሆን ኖሮ፣ ለሁሉም ሰው ገንዘብ እሰጥ ነበር።

1

እኔ ተሽከርካሪ ብሆን ኖሮ፣ ሰዎችን ያለ ምንም ክፍያ (በነፃ) አጓጉዝ ነበር።

2

እኔ አዳኝ ብሆን ኖሮ፣ የማድነው ፀጉር የሌላቸውን እንስሳት ብቻ ነበር።

3

እኔ አይጥ ብሆን ኖሮ፣ በደንብ ወፍሬ ድመቷን አባርራት ነበር።

4

እኔ ሕፃን ብሆን ኖሮ፣ የማለቅሰው ውድ ለሆኑ ነገሮች ብቻ ነበር።

5

እኔ ድመት ብሆን ኖሮ፣ ይበልጥ ለመወፈር አይጦችን እበላ ነበር።

6

እኔ ዶሮ ብሆን ኖሮ፣ ለሰዎች የወርቅ እንቁላሎችን እጥል ነበር።

7

እኔ ለማኝ ብሆን ኖሮ፣ ሳንቲሞችን አልቀበልም ነበር።

8

እኔ ሐኪም ብሆን ኖሮ፣ ሰዎችን በጥፊ እያከምኩ እፈውሳቸው ነበር

9

እኔ ቄስ ብሆን ኖሮ፣ ሰዎችን ሁሉ ወደ መንግስተ ሰማያት እወስዳቸው ነበር።

10

እኔ ቢንቢ ብሆን ኖሮ፣ በአልጋ አጎበር ውስጥ እተኛ ነበር።

ልጆች! "እኔ ብሆን ኖሮ..." እያልን ያደረግነው ጉዞ ምንኛ ያስደስታል! በምናባችን ክንፍ እየበረርን ዶሮ፣ ሐኪም፣ እንዲያውም ቢንቢ ሆነን አይተናል።

11
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
እኔ ብሆን ኖሮ
Author - Kabubbu pilot site
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration - , Alice Toich, Catherine Groenewald, Cathy Feek, Jano Strydom, Karen Lilje, Marleen Visser, Natalie Propa, Rebecca Riley, Rob Owen, Wiehan de Jager
Language - Amharic
Level - First paragraphs