ስሜቶች ይመጣሉ ይሄዳሉ
Mimi Werna

አዳ አስቂኝ ታሪክ ስለሰማች እየሳቀች ነው።

ፈገግ ብላለች።

አዳ ምን ይሰማታል?

1

ጊሳ በቁጣ ስሜት እየተዋጠ ነው።

ፊቱ ላይ ቁጣ እየተነበበበት ነው።

ለምን ተናደደ?

2

ዩአዱ ጨለማ ይፈራል።

ሁሉም ሰው አንዳንድ ጊዜ ፍርሃት ይሰማዋል።

ነገር ግን ዩአዱ እርዳታ መጠየቅ ይችላል።

3

ቺዱቤም ስለ ትምህርት ቤቱ ሥራው ይጨነቃል።

ለአስተማሪው መንገር ይችላል።

እርዳታ መጠየቅ ይችላል።

4

ሉሻን እየተጫወተች ነው!

አንዳንድ ጊዜ ሞኝ መሆን ችግር የለውም።

5

ዩሮ እያዘነ ነው።
ማልቀስ ችግር የለውም።
ስሜቶች ይመጣሉ ይሄዳሉ።

6

አያተር በደስታ አየፈነጠዘ ነዉ ።

ደስተኛ ነው።

ስሜቶች ይመጣሉ ይሄዳሉ።

7

ሃዲዛ አሰልቺ ነች።

የምትሰራዉን ማግኘት አለባት።

8

አዮ ተናዷል።

ተበሳጭቷልም።

ቁጣ አስቸጋሪ ስሜት ነው።

9

ላቤክ በጣም ተደስታለች።

የደስታዋ መንስኤ ምንድን ነው?

እናቴ የምትወደውን ምግብ ስላዘጋጀችላት።

10

ዘጌን እንቅልፍ ወሰዶትነበር።

በጣም ደክሞትም ነበር።

"ቆይ ግን 'እንቅልፍ' የሚለው ስሜት ነው?" ሲል ኤፌሶን ጠየቀ።

11

ፌ ግራ ተጋብቷል!

ለጥያቄው መልስ መስጠት ትችላለህ?

12

ቴጋ መደነቅና ድንጋጤ እየተሰማው ነው።

አንዳንድ ሐሜቶችን ሰምቷል።

እውነት ነው?

13

የቦ ታምማለች።

በጣም ተጨንቃለች ሃዘንም ተሰምቷታል።

ጥሩ ስሜት እንዲሰማት መድኃኒትና እረፍት ያስፈልጋታል።

14

ሴክየን እርካታ እየተሰማት ነው።

የቤት ስራዋን በአንድ ጊዜ ጨርሳለች።

አሁን መጫወት ትችላለች።

ሥራዋን ጨርሳለች።

አሁን መጫወት ትችላለች.

15

ቫንዴፋን ዛሬ የቤት ውስጥ ሥራዎች የሉትም።

ለሴክን ሁለት አውራ ጣት እያሳየ ነው።

"ጥሩ ስራ ነው፣ አሁን እንጫወት!" አለ።

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ስሜቶች ይመጣሉ ይሄዳሉ
Author - Mimi Werna
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration - , Joe Werna
Language - Amharic
Level - First paragraphs