የመሳል ህልሞች
Steshka Tiffanie Stephen
Masari Henry

በክሪስታል ክላሲክ አካዳሚ ውስጥ ኒሙታባን የሚባል ወጣት ልጅ ነበር።

መሳል ይወድ ነበር፣ ነገር ግን ወላጆቹም ተስፋ ቆርጠውበታል።

1

ሁሉንም የማስታወሻ ደብተሮቹን ለመሳል ይጠቀም ነበር።

ወላጆቹና መምህራኑ ቀጥተውታል።

ነገር ግን ኒሙታባን መሳል አላቆመም።

2

ወላጆቹም የትምህርት ቤት አስተማሪዉ የነበሩትን ሚስተር ንጋቮን አመጡለት።

በጣም ደግ ሰው ነበሩ። ኒሙታባን ከትምህርቱ በኋላ እንዲስል ፈቅደዉለታል።

3

ሚስተር ንጋቮ መጽሐፍትን፣ ሰሌዳዎችን እና ባለቀለም ቀለሞችን እንዲስል አደረገለት።

ኒሙታባን እጅግ በጣም ጥሩ አርቲስት ሆነ። በእያንዳንዱ የትምህርት ቤት ዉጤትም ጥሩ ውጤት አስመዝግቧል።

4

በየዓመቱ ኒሙታባን በትምህርት ቤቱ የሽልማት ቀን ብዙ ሽልማቶችን ይቀበል ነበር።

ሌሎች ተማሪዎች እሱን ያደንቁታል እና እንደ እሱ መሆን ይፈልጉም ነበር።

5

ሲያድግም፣ ኒሙታባን በናይጄሪያ ውስጥ ካሉት ምርጥ አርቲስቶች መካከል አንዱ ነበር!

በጣም ጠንክሮ ሰርቶ ብዙ ሽልማቶችን እና ኮንትራቶችን አሸንፏል።

6

ኒዩሙታባን ለራሱ "ለሌሎች ስነጥበብ ለሚወዱ ነገር ግን የሳይንስ ትምህርቶችን ለመማር ለሚገደዱ ልጆች ምን ማድረግ እችላለሁ?" ብሎ አሰበ።

7

የኒሙታባን የስነጥበብ ማዕከልን አቋቋመ! በማዕከሉ ልጆች ከትምህርት ቤት በኋላ ስነጥበብን መማር እና ተሰጥኦአቸውን ማዳበር ይችላሉ።

ኒሙታባን አርቲስቶችን ለማበረታታት የስነጥበብ ውድድሮችን አዘጋጅቷል።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የመሳል ህልሞች
Author - Steshka Tiffanie Stephen
Translation - Tesfamichael Hailu,Natnael Argaw
Illustration - Masari Henry
Language - Amharic
Level - First paragraphs