የአፍሪካ ቀን በትምህርት ቤቴ
Peter Msaka
Japhet Katuma

በየዓመቱ በትምህርት ቤቴ የአፍሪካ ቀንን እናከብራለን። በዚህ ዓመት ይህንን ቀን ነገ እናከብራለን።

እኔና ጓደኞቼ የአፍሪካ የወንዶችን ልብስ ለማሳየት ተዘጋጅተናል።

1

ጓደኞቼን በከተማው ውስጥ ወደሚገኘው ቁጥር አንድ የልብስ ስፌት ወሰድኳቸው።

ማሉሜ ብለን እንጠራዋለን፤ ትርጉሙም አጎት ማለት ነው።

2

ማሉሜ የአፍሪካ ወንዶችን የአለባበስ ዘይቤዎች ሁሉ ያውቃል።

ፍላጎታችንን በማሟላቱ ሁላችንም ደስተኞች ነን።

3

የማላዊ ካሊድዌ ልብስ አድርጎልኛል።

ይዘቶች እና ተመሳሳይ ቁምጣ ያለው ክሬም ነጭ ሸሚዝ ነው።

4

ጓደኛዬ ሴካኒ፣ ታዋቂውን የአፍሪካ ዳሺኪን ይልበስ።

ሰማያዊ ሲሆን ባለብዙ ቀለም ጥልፍ አለው።

5

ያሚካኒ በምስራቅ አፍሪካ ኪቴንጅ ውስጥ ቀላል ይሆናል።

ብርቱካናማ እና አረንጓዴ የቼክ ቅርጽ ያላቸው ቅጦች አሉት።

6

ማዬሶ የምዕራብ አፍሪካዊውን አባዳን ያሳያል።

የእሱ ቢጫ ሲሆን ከፊት ለፊቱ አረንጓዴ ካሬ ይዘቶች አሉት።

7

ፒሊራኒ በሴኔጋል ካፍታን ውስጥ ረጅም ትመስላለች።

ሰማያዊ ይዘቶች ያሉት ብርቱካናማ ልብስ ነው።

8

ሲዬኒ ቀለል ያለ ሰማያዊ የኬንያ ሳፋሪ ልብስ ለመልበስ ወስኗል።

በጣም ኦፊሴላዊ ይመስላል።

9

ማጆኒ የኤስዋቲኒ ሊሂያን ትለብሳለች።

የደማቅ ቀለሞች ድብልቅ ነው።

ሁላችንም በተለያዩ የአፍሪካ አለባበሶቻችን እንኮራለን።

10
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የአፍሪካ ቀን በትምህርት ቤቴ
Author - Peter Msaka
Translation - Tesfamichael Hailu,Natnael Argaw
Illustration - Japhet Katuma
Language - Amharic
Level - First paragraphs