የእንስሳት ውድድር
Rukia Odondo
Rob Owen

ንጉሥ ነብር ሁሉንም እንስሳት ለውድድር ጠራ። ይህ ውድድር በየዓመቱ ይካሄድ ነበር።

በየዓመቱ ንጉሥ ነብር እንስሳት የሚሳተፉበት አዲስ ጨዋታ ያዘጋጅ ነበር።

1

በዚህ ዓመት እንስሳቱ ጦራቸውን በተቻለ መጠን ከፍ አድርገውና በተቻለ መጠን መወርወር ነበረባቸው። እያንዳንዱ እንስሳ በራሱ መንገድ ይለማመዱ ነበር።

አንዳንድ እንስሳት ማን እንደሚያሸንፍ እርስ በእርሳቸው ይወራረዱ ነበር።

2

የሚጠበቀው ቀን ደረሰ። እንስሳት ዝሆን፣ የዋርቶግ ወይም የዝንጀሮ ቡድን ነበሩ።

ንጉሥ ነብር ለእያንዳንዱ መሪ "ይህን ጦር በተቻለ መጠን ከፍ አድርገህ እንድትወረውር እፈልጋለሁ" አላቸው።

3

ዝሆን፣ዋርቶግ እና ዝንጀሮ ውድድሩ ወደሚካሄድበት መድረክ ሲቃረቡ እያንዳንዱ ቡድን ጮክ ብሎ ጮኸ።

4

የቡድኑ አባላት እርስ በእርሳቸው መቀለድ ጀመሩ። እንዲሁም ዝሆን፣ ዋርቶግ እና ዝንጀሮውን የሚደግፉ እና የሚያወዳድሩ ዘፈኖችን ዘፈኑ።

ዝንጀሮው ሳቀ፣ ዋርቶግ ፈርቶ ነበር፣ እና ዝሆን አሾፈባቸው።

5

ዝሆን የመጀመሪያው ወረወረ። ጦሩን በተቻለው መጠን ከፍ አድርጎ ለመወርወር ኃይሉን ሁሉ ተጠቅሟል።

ጦሩ በጣም ሩቅ አረፈ። ንጉሥ ነብር ለዝሆን እንኳን ደስ አለህ አለው ፣ የዝሆን ቡድንም በደስታ ጮኸ።

6

ከዚያም ዋርቶግ ጦሩን በጥንቃቄ ወረወረው።ጦሩ የዝሆን ጦርን ምልክት በጣም ርቆ አረፈ።

ዝሆን ማልቀስ ጀመረ!

7

ቀጥሎም ዝንጀሮ ጦሩን በጣም አርቆ ወረወረው። ዝሆን ሆነ ዋርቶግን አሸንፏል። ባቢሎን "አዎ! ሁለቱንም አሸነፍኳቸው" አለ።

የዝንጀሮ ቡድን ጨፈረ። ዝንጀሮ ውድድሩን በማሸነፉ ሽልማቱን አግኝቷል።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የእንስሳት ውድድር
Author - Rukia Odondo
Translation - Tesfamichael Hailu, Yeabsra Asfaw
Illustration - Rob Owen, Salim Kasamba
Language - Amharic
Level - First paragraphs