ጉንዳን እና ዝሆን
Sicelo Hlamandana

አንድ ቀን ጠዋት እንስሳቱ ንጉሣቸውን ለመምረጥ ተሰበሰቡ።

የተለያዩ እንስሳትና ነፍሳት ወደ ስብሰባው መጡ። ነገር ግን።

ትላልቅ እንስሳት የሆኑት ዝሆኖች በስብሰባው ላይ አልተገኙም። በዚህ ሁሉም እንስሳት ተገረሙ።

1

ስብሰባው ያለ ዝሆኖች ቀጥሏል።

"ዝሆኖቹ ባይኖሩም እንኳ ምርጫውን እናካሂዳለን። ዛሬ ንጉሣችንን ማወቅ አለብን" አለች ጉጉት።

2

እንስሳቱ ጉንዳንንእንደ አዲሱ ንጉሥ አድርገው መረጡት።

ጉንዳን ቢፈራም መሪ ለመሆን ተስማማ።

ጉንዳንም "ብዙ ስራዎችን የሚጠይቅ ትልቅ ኃላፊነት ነው" ብሎ አሰበ።

3

ጉንዳን ንጉሥ ሆኖ መመረጡን የሚገልጸው ዜና በፍጥነት ተሰራጨ።

ይህ ዜና ወደ ዝሆኖች ልዑል ጆሮ ደረሰ። በጣም ተናደደ።

4

የዝሆኖች ልዑል ምግብ ለመፈለግ ወደ ጫካ ሄደ።

ኃያል ነበር እና ሌሎችን አያከብርም ነበር፣ በተለይም እንደ ጉንዳኖች ያሉ ትናንሽ እንስሳትን አያከብርም።

የጉንዳኖቹን ግዛት መውረሩም ግድ አልሰጠውም።

5

ወጣቱ ዝሆን እያለቀሰ ንጉሥ ጉንዳንን ይቅርታ ጠየቀ።

በዚያን ቀን ልዑሉ አዝኖና ተርቦ ወደ ቤቱ ተመለሰ።

6

ዝሆኖቹ ልዑላቸው ወደ እነሱ በመመለሱ ደስተኞች ነበሩ።ጉንዳ ንጉሥ መሆኑ ግድ አልነበራቸውም።

ጉንዳኖቹ በጣም ትንሽ ቢሆኑም እንኳ በጥሩ ሁኔታ ይገዙ ነበር።

7
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጉንዳን እና ዝሆን
Author - Sicelo Hlamandana
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration -
Language - Amharic
Level - First sentences