የእኔ ዓይነ ስውር ምርጥ ጓደኛ
Yamkela Maqwara
Canva AI

በትምህርት የመጀመሪያ ቀን፣ ሾላ ረጅም ጥቁር ዘንግ (በትር) ይዞ ነበር።

ሌሎች ተማሪዎች ይህ ነገር እንግዳ (አዲስ) ሆኖባቸዋል።

1

መምህርት ፊክሌፊ ሾላ (Xola) ዓይነ ስውር ሆኖ እንደተወለደ ለክፍሉ ተማሪዎች አስረዳች።

በትምህርት ቤቱ ውስጥ መንገዱን ፈልጎ ለማግኘት ዘንግ (በትር) እንደሚጠቀምም ገለጸችላቸው።

2

ተማሪዎቹ ሾላ ለምን ጥቁር መነጽር እንደሚያደርግ መረዳት ጀመሩ።

መምህርቷ በመቀጠል ተማሪዎቹ ሾላን እንደ አንዱ (እንደ እራሳቸው) አድርገው ሊያዩት እንደሚገባ አስረዳች።

3

ሊዞ እና ሌሎች ወንዶች ልጆች የሾላን ዘንግ (በትር) ለመስረቅ ሲያሴሩ ዞላ በድንገት ሰማቻቸው።

ልጆቹ አዲሱን ተማሪ ለማላመድ (ለመጫወት) ይህ ጥሩ መንገድ እንደሆነ አስበው ነበር።

4

ዞላ ይህንን ስትሰማ፣ ሾላን ከጉልበተኞች ለመከላከል ሮጣ አጠገቡ ተቀመጠች።

ሊያደርጉት ያሰቡት ነገር የሚያስከትለውን አደጋ ነገረቻቸው። ልጆቹም ለሾላ ከልብ ይቅርታ ጠየቁት።

5

ጓደኞቹ ተቀምጠው ስለ እግር ኳስ ፍቅራቸው፣ ስለ ስዕል መሳል እና አኒሜሽን (ተንቀሳቃሽ ምስሎችን) ስለ መመልከት ተጨዋወቱ። ከዚህ ውይይት በመነሳት በመካከላቸው ብዙ የሚያመሳስሏቸው ነገሮች እንዳሉ ተገነዘቡ።

6

ስለ ልዩነቶቻቸውም ጭምር ተጨዋወቱ። ዞላ የጓደኛዋን ጥቁር መነጽር በማድነቅ አሞካሸችው። ይህ ጓደኝነት እርስ በእርሳቸው አድናቆትንና ክብርን የሚሰጡ የእኩዮች ስብስብ (መረብ) እንዲፈጠር አደረገ።

7

ለሾላ በጣም አስደሳች ቀን ነበር፤ በአዲሱ ትምህርት ቤቱ ውስጥ ከአዲሷ አፍቃሪ ጓደኛው ከዞላ ጋር የደህንነት እና የመልካም አቀባበል ስሜት ተሰማው።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የእኔ ዓይነ ስውር ምርጥ ጓደኛ
Author - Yamkela Maqwara
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration - Canva AI
Language - Amharic
Level - First paragraphs