ስግብግቡ ኤሊ እና አስማታዊው መጥረጊያ
Eno Boatemaa Dwomoh
Eno Boatemaa Dwomoh

ለረጅም ጊዜ የቆየው ድርቅ በጫካው ውስጥ የነበሩትን የውኃ አካላት በሙሉ አደረቃቸው።

በጫካው ውስጥ ለሚኖሩ እንስሳት ሁሉ ሕይወት በጣም አስቸጋሪ ሆነባቸው።

1

የእንስሳቱ ንጉሥ የሆነው አንበሳ፣ ሁሉም መፍትሄ እንዲፈልግ አዘዘ። 'ያንን አስማታዊ መጥረጊያ ፈልጉ!' ሲል ትዕዛዝ አስተላለፈ።

ይህ መጥረጊያ ምግብና ውኃ እንደሚያመጣላቸው በጽኑ ያምን ነበር።

2

ብልጡ ጥንቸል የታደለ ነበር!

አስማታዊውን መጥረጊያ አግኝቶ ወደ አንበሳው ዘንድ ይዞት ሄደ።

3

አንበሳውም፣ 'አስማታዊ መጥረጊያ ሆይ! ምግብ አምጣልን!' ሲል አዘዘ።

ወዲያውኑ ለእንስሳቱ ሁሉ የሚበቃ የተትረፈረፈ ምግብ ተገኘ።

4

አንድ ምሽት፣ ስግብግቡ ኤሊ በድብቅ ወደ አንበሳው ቤተ መንግሥት ዘልቆ በመግባት አስማታዊውን መጥረጊያ ሰረቀ።

መጥረጊያውን ከአንድ ዛፍ ሥር ደብቆ፣ ለራሱ ብቻ መጠቀም ጀመረ።

5

ያለ አስማታዊው መጥረጊያ፣ በጫካው ውስጥ እንደገና አስከፊ ረሃብ ተከሰተ።

ብዙ እንስሳት በራብ ምክንያት ደከሙና እየዛሉ መጡ።

6

ጉጉው ሸረሪት ስግብግቡን ኤሊ ተከታትሎት ምስጢሩን ደረሰበት።

ስግብግቡ ኤሊ ጉጉው ሸረሪት እንዳየው ሲያውቅ ደነገጠ። ከዚያም መጥረጊያው በሮ እንዲሄድ አዘዘው።

7

አስማታዊው መጥረጊያ ተሰወረ፤ ስግብግቡ ኤሊም አብሮት ጠፋ!

ከዚያ በኋላ ቤተሰቦቹ ዳግመኛ አላዩትም።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ስግብግቡ ኤሊ እና አስማታዊው መጥረጊያ
Author - Eno Boatemaa Dwomoh
Translation - Tesfamichael Hailu,Natnael Argaw
Illustration - Eno Boatemaa Dwomoh
Language - Amharic
Level - First paragraphs