ቡንቲ እና ቡብሊ
Sorit Gupto
Sorit Gupto

ቡቲ ከቢራቢሮዎች ጋር መጫወት ትወዳለች።

1

እና ከወፎች ጋር።

2

በወረቀት ጀልባዎች መጫወት ትወዳለች።

3

እሷም የአሸዋ ቤተ መንግሥቶችን መሥራት ትወዳለች።

4

ቡንቲ ወደ ቤት ስትመለስ እናቷ ጽዳት እንድታደርግ ጠየቋት።

እምቢ አለች።

5

"ሳሙና እጠላለሁ!" ብላ ጮኸች።

6

አንድ ሌሊት ሕልም አየች።

ጀርሞቹ በቤተ መንግሥቷ ዙሪያ ገብተው እያጠቁዋት ነው።

7

ቡንቲ በጀርሞች እየተባረረች ነው።

ሕይወቷን ለማዳን እየሮጠች "እርዱኝ እርዱኝ!" ብላ ትጮኻለች።

8

በድንገት፣ የሳሙና ንጉሥ ቡብሊ ብቅ አለ። "ቡንቲ፣ አትፍሪ" አለ። "ሂዱና ጀርሞቹን አጥፋቸው!" አለ የሳሙና ንጉሥ የአረፋ ሠራዊቱን አዘዘ።

9

የአረፋው ሠራዊት ጀርሞቹን አባረሩዋቸው ።

10

በአሁኑ ጊዜ ቡንቲ ሳሙና መጠቀም ትወዳለች፣ እራሷንም ታጸዳለች።

11
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ቡንቲ እና ቡብሊ
Author - Sorit Gupto
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration - Sorit Gupto
Language - Amharic
Level - First sentences