ጉጉ ልጅ
Tshepiso Mogaswa

አሞ የሚባል ወጣት ልጅ ነበር።

ስለ ተፈጥሮ የማወቅ ጉጉት ነበረው።

1

ዛፎች ላይ ተንጠላጥሎ እና ከዛፎች ስር ተቀምጦ ማሰብ ይወድ ነበር።

2

አንድ ቀን ሀብሐብ በረጃጅም ዛፎች ላይ ለምን አይበቅልም ብሎ አሰበ።

3

እና "ለምንድነው የቤሪ ፍሬዎች መሬት ላይ የማይበቅሉት?" ብሎ አሰበ።

4

ሀሳቡን እንደጨረሰ አንድ የቤሪ ፍሬ ራሱ ላይ ወደቀ።

5

ደግነቱ ሐብሐብ አልነበረም የወደቀበት።

ሊጎዳው ይችል ነበር።

6

እዚያ ተቀምጦ ሁሉንም ነገር በተፈጠረበት መንገድ አደነቀ።

7
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጉጉ ልጅ
Author - Tshepiso Mogaswa
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration - , Andrews Opoku Antwi, Brian Wambi, Kenneth Boyowa Okitikpi, Mekasha Haile, Michelangelo Quaye Anang, Wiehan de Jager
Language - Amharic
Level - First words