የአካባቢያችንን ንጽሕና የሚጠብቁት ትናንሽ መሪዎች
Ruth Asuquo

ሉምባዚ ጥሩ ቦታ መሆን ትችል ነበር፣ ነገር ግን ስለ አካባቢው ያለው ሁሉም ነገር የተሳሳተ ነበር።

በየቦታው የተሰበሩ ጠርሙሶች እና በጎዳናዎች ላይ የተጣሩ ወረቀቶች ነበሩ ። እንዲሁም አየሩ በጣም መጥፎ ጠረን ነበረው።

1

ህጻናት በተሰበሩ ጠርሙሶች ይቆስላሉ።

2

ነፋሻማ ሲሆን፣ የተጣሉ ወረቀቶች እየተነሱ በዛፎች እና ጣሪያዎች ላይ ይንጠለጠላሉ።

ይህም ብዙ ሰዎች ሉምባዚን እንዳይጎበኙ አድርጓል።

3

አንድ ቀን የ9 ዓመቱ ቺኬ አንድ ሀሳብ ለጓደኞቹ አካፈለ።

"አካባቢያችንን በጋራ እናፅዳ፣ የተሰበሩ ጠርሙሶችን ጠርገን ማንሳት እንችላለን እንዲሁም ለቤታችን እና ለመንገዶቻችን የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችን መስራት እንችላለን።"

4

"ይህ ንጹህ እንድንሆን ይረዳናል ፣ ሌሎች ማህበረሰቦችን እንዲጎበኙን ይስባል። "ሲል ቺኬ ቀጠለ።

5

ይህን እየተናገረ እያለ ፣ ኦቢ "የተበላሹትን ጠርሙሶች በጥንቃቄ አነሳለሁ፣ እኛን በማይጎዱበት ቦታ አስቀምጣቸዋለሁ።" አለ።

6

ፊሊክስም "በቤቴ ውስጥ ካሉት አሮጌ ባልዲዎች አንዱን አመጣለሁ ስለዚህ እንደ ቆሻሻ መጣያ እንጠቀምበት።" አለ።

7

በየቀኑ አብረው መስራት ጀመሩ።

ከዚያን ቀን ጀምሮ ሉምባዚ ሁሉም ሰው የሚቆይባት ጤናማ እና ደህንነቷ የተጠበቀ ቦታ ሆነች።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የአካባቢያችንን ንጽሕና የሚጠብቁት ትናንሽ መሪዎች
Author - Ruth Asuquo, Gideon Eyo
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration -
Language - Amharic
Level - First paragraphs