ቶም የሙዝ ነጋዴ
Humphreys Odunga

ቶም የበሰለ ሙዝ በትሪ ይዟል።

1

ቶም ሙዝ ለመሸጥ ወደ ገበያ ሄደ።

2

በገበያዉ ላይ ያሉ ሰዎች ፍራፍሬ እየገዙ ነው።

3

ግን ማንም የቶምን ሙዝ አይገዛም።

ሰዎቹ ከሴቶች ፍራፍሬ መግዛት ይመርጣሉ።

4

"በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ሴቶች ብቻ ናቸው ፍራፍሬ የሚሸጡት" ይላሉ።

"ይህ ምን አይነት ሰው ነው?" እያሉ ሰዎች ይጠይቃሉ።

5

ቶም ግን ተስፋ አልቆረጠም።

"ሙዝዬን ግዙ! ጣፋጭ የበሰለ ሙዝዬን ግዙ!" እያለ ይጣራል።

6

አንዲት ሴት ከትሪ ውስጥ የሙዝ ዘለላ መረጠች።

እናም ሙዙን በጥንቃቄ ተመለከተች።

7

ሴተዮዋም ሙዞቹን ግዛች።

8

ብዙ ሰዎች ወደ ድንኳኑ መጡ።

እናም የቶምን ሙዝ ገዝተው በሉ።

9

ብዙም ሳይቆይ ትሪው ባዶ ሆነ።

ቶምም ያገኘውን ገንዘብ ቆጠረ።

10

ከዚያም ቶም ሳሙና ፣ ስኳር እና ዳቦ ገዛ።

እቃዎቹንም በትሪው ውስጥ አስቀመጣችው።

11

ቶም ትሪውን በራሱ ላይ አስቀምጦ ወደ ቤቱ ሄደ።

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ቶም የሙዝ ነጋዴ
Author - Humphreys Odunga
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration - , Atilabachew Reda
Language - Amharic
Level - First sentences