ከባድ ችግር ያለበት ሰው
Ursula Nafula

ማንዱ ከአያቶቹ፣ ከአክስቱ እና ከአጎቱ ጋር ይኖር ነበር። ዶሮ፣ ፍየል፣ በግ እና አሳማ ነበረው።

ዶሮ በትንሽ ጎጆ ውስጥ አለች። ፍየሉ፣ በግ እና አሳማው እያንዳንዳቸው በግድግዳው በኩል ታስረዋል። አያቶቹ አሁንም ደህና ነበሩ። አክስት እና አጎቱ በስራ ይራዳሉ።

1

ይህ ከጥቂት አመታት በኋላ ተለወጠ። የማንዱ አያቶች አረጁ እና በደንብ መስማት ወይም ማየት አልቻሉም።

አክስቱ ታመመች እና ቤቱን ማጽዳት አልቻለችም።

አጎቱ ሁል ጊዜ ይተኛሉ እና እንስሳትን ለመመገብ መርዳት አልቻሉም።

2

እንስሳቱ ስለተራቡ ብዙ ድምፅ ያሰማሉ።

አክስቷ ቤቱን ስላላጸዳችው በጣም ቆሽሾ ነበር።

ማንዱ ሁል ጊዜ ይደክመው ነበር። ለሁሉም ምግብ ፍለጋ በየቀኑ መውጣት ነበረበት።

3

ማንዱ ከዛ በኋላ ሁኔታውን መቋቋም አልቻለም። መፍትሄ ለማግኘት አረጋውያን አያቶቹን ጠየቃቸው። አያቶቹ ስላልሰሙት ደስተኛ አልነበረም።

የታመመች አክስቱ "እኔ የምፈልገው ሌሊት መተኛት እና በጠዋት መነሳት ብቻ ነው" አለች።

4

ሰነፍ አጎቱ "እንስሳቱን ሽጠህ ለአያቶችህ እህል ግዛ። ከዛ ተኝተው አያስቸግሩህም" አለው።

ማንዱ ተናደደ። እሱም "አጎቴ እንስሳትን መሸጥ እንደማልችል ታውቃለህ። ያለኝ ሀብት እነሱ ብቻ ናቸው።" አለው።

5

አንድ ምሽት ማንዱ አይኑን ሳይከድን ተኛ። ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አለው ተብሎ የሚታመን አንድ ጠቢብ ሰው አስታወሰ።

ማንዱ በፍየሉ፣ በግ እና በአሳማው ላይ ገመድ አስሮ እና ዶሮዋን በመሸከም እንስሳዎቹን ወስዶ ጠቢቡን ጎበኘ።

6

ማንዱ ደክሞና ተርቦ የጠቢቡ ሰው ቤት ደረሰ።

ችግሮቹንም ለጠቢቡ ከገለጸ በኋላ ጠቢቡም "እረዳሃለሁ ነገር ግን እኔ ያልኩትን አድርግ" አለው።

ማንዱም "ችግሬን ለመፍታት ማንኛውንም ነገር አደርጋለሁ" ሲል መለሰ።

7

ጠቢቡም ሰው "እንስሳቱን እዚህ ትተህ ወደ ቤትህ ተመለስ" አለው።

ማንዱም "እኔ ግን ከእንስሳቶቼ ጋር ለረጅም ጊዜ ኖሬአለሁ። ያለኝ ሀብት እነሱ ብቻ ናቸው።" አለው።

8

ጠቢቡም "እንደምረዳህ ነግሬሃለሁ ግን እኔ ያልኩትን አድርግ" አለው።

ማንዱ ለችግሩ መፍትሄ ያስፈልገዋል። ከብቶቹን ትቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ።

9

ቤቱ በጣም ጸጥ ያለ እና ባዶ ነበር። ሁሉም እንስሳቱ ናፍቀዋቸው ነበር። የማንዱ አያቶች ከፍየሉ ወተት ስላልነበራቸው ቅሬታቸውን አሰሙ።

አጎቱ "እኛ በጣም ድሆች ነን ሁሉም እየሳቁብን ነው" አለ።

10

ማንዱ ቅሬታዎቹን መቋቋም አልቻለም። ከዚህም በተጨማሪ እንስሳቱ ናፈቁት።

ምክር ለመጠየቅ ወደ ጠቢቡ ተመለሰ። "የእኔ እንስሳት በቤቱ ውስጥ ከሌሉ ህይወት በጣም የተለየ ነው፣ ዘመዶቼ በጣም ይናፍቋቸዋል።"

11

ጠቢቡም "እረዳሃለሁ ነገር ግን እንደነገርኩህ አድርግ፤ ወደ ቤትህ ሂድና አያቶችህን ከቤት አውጣ" አለው።

ማንዱ "እንዴት ላደርገው እችላለሁ? አያቶቼ ናቸው እና በእኔ ላይ ጥገኛ ናቸው" አለ።

12

በመጨረሻ ማንዱ ወደ ቤት ሄዶ እንደታዘዘው አደረገ። የአእምሮ ሰላም አልነበረውም።

አያቶቹ የሚሄዱበት ቦታ አልነበራቸውም። በነገሮች ላለመደናቀፍ እየሞከሩ ዞሩ። ቀን ቀን ሙቀቱ እና በሌሊት ቅዝቃዜ አስቸግሯቸዋል።

13

የታመመች አክስቱ "አትጣሉኝ!"

ሰነፍ አጎቱ "እኔንም አትጣሉኝ!" እያሉ አለቀሱ።

14

ማንዱ ከዚህ በላይ መቋቋም አልቻለም። ግራ ተጋብቶ ተናዶ ወደ ጠቢቡ ተመለሰ።
"ይህ ለአንድ ሰው ከአቅሙ በላይ ነው የተሻለ መፍትሄ ስጠኝ" እያለ አለቀሰ።

15

ጠቢቡም ሰው "እነሆ እንስሶቻችህን ወደ ቤት ውሰድ እና አያቶችህን ወደ ቤት መልሳቸው" አለው።

ማንዱ እንደተባለው አደረገ። አክስቱም "ቤቱን አጸዳለሁ" አለች።

አጎቱ ስንፍናን ትቶ ማንዱን በሥራ ረዳው። ሁሉም እንደገና ተደሰቱ።

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ከባድ ችግር ያለበት ሰው
Author - Ursula Nafula
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration - , Abraham Muzee
Language - Amharic
Level - Longer paragraphs