ጀግናው ኤሊ
Ntombifuthi Ncwayiba

ከረጅም ጊዜ በፊት የዱር እንስሳት ውሃ አለቀባቸው።

በየቦታው ቢመለከቱም ምንም አላገኙም።

1

ለችግራቸው መፍትሄ ለማግኘት ተሰበሰቡ። ከቀበሮ በስተቀር ሁሉም እንስሳት በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል።

ቀበሮ፣ "እንዴት ከሚሸት ኤሊ ጋር ስብሰባ ላይ እገኛለሁ?" አለ።

2

በስብሰባው ላይ እንስሳት ጉድጓድ ለመቆፈር ተስማሙ።

አጋዘን "ጕድጓዳችን ጥልቅና ሰፊ ይሆናል፤ ሲሞላ ውኃ አያልቅብንም" አለ።

3

እየዘፈኑ እና እየጨፈሩ በመፈራረቅ ጉድጓዱን ቆፈሩ።

በመጨረሻም ውሃ መሬቱን ሰብሮ ጉድጓዱን ሞላው።

በጣም ተደስተው ነበር። እንደዚህ አይነት ጣፋጭ እና አዲስ ውሃ ቀምሰው አያውቁም።

4

ከዚያም አንድ ቀን እንስሳቱ አንድ እንስሳ በውሃ ውስጥ እየዋኘ እንደሚያቆሽሸው ተገነዘቡ።

እየተፈራረቁ ጉድጓዱን መጠበቅ ጀመሩ።

5

ጥንቸል ጉድጓዱን በመጠበቅ ላይ ነበረች። ቀበሮ ከሚዘለው ገመዱ ጋር አብሮ መጣ።

"እዚህ ምን እየሰራህ ነው?" ሲል ቀበሮ ጠየቀ።

ጥንቸል "ውሃችንን እየጠበኩ።'' አለች።

6

ቀበሮው ጥንቸል ከእሱ ጋር እንድትጫወት ጠየቃት።

ጨዋታው አንድ ተጫዋች በገመድ ታስሮ አይኑን ጨፍኖ እስከ አንድ ሺህ መቁጠር ነው።

ጥንቸልም ለመጫወት ተስማማ።

7

ቀበሮ ጥንቸልን አስሮት ጥንቸል አይኑን ጨፍኖ መቁጠር ጀመረ።

ቀበሮ ከጉድጓዱ ጠጥቶ ዋኘ።

ከዛ በኋላ ቀበሮ ውሃ ወስዶ ሄደ። ጥንቸል አሁንም ይቆጠር ነበር።

8

ጥንቸል ቆጥሮ ጨርሶ አይኑን ከፈተ።

ቀበሮ የትም የለም።

ጥንቸል ሌሎቹ እንስሳት መጥተው እንዲፈቱት ጮኸ።

9

እንስሳቱ እየተፈራረቁ ጉድጓዱን ሲጠብቁ ሁሉም ቀነሮን መያዝ አልቻሉም።

ኤሊ "እስኪ እንድከታተል ፍቀዱልኝ" አለ። ቀበሮን ለመጠበቅ ወደ ጉድጓዱ ዘልቆ ገባ።

10

ቀበሮ ሲደርስ "እዚህ ማንም የለም!" ብሎ አሰበ። ከዛም መጠጣት ጀመረ።

ምላሱን የነከሰው ነገር እንዳለ ተሰማው። ከዚያም ወደውሃው ውስጥ ተሳበ።
ቀበሮ ሲያለቅስ እና ውሃውን ሲረጭ የሰሙ እንስሳቶች እየሮጡ መጡ።

11

እንስሳቱ ቀበሮን አሰሩት።

ኤሊ ቀበሮን "ሁላችንን ስለበደልክ ትቀጣለህ" አለው። እንስሳቱ ኤሊ ጀግና ብለው አወደሱት።

ከዚያን ቀን ጀምሮ ያለምንም ግርግር በደስታ ንፁህ ውሃ መጠጣት ጀመሩ።

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጀግናው ኤሊ
Author - Ntombifuthi Ncwayiba
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration -
Language - Amharic
Level - First paragraphs