የታክጋሎ የሙዚቃ ተሽከርካሪ ወንበር
Diana Tebeila

ታክጋሎ ማለት ደስታ ማለት ነው።

ታክጋሎ ዊልቸር የመትጠቀም ልጅ ነች።

ቤተሰቦቿ እና ጓደኞቿ በጣም ይወዷታል።

1

ታክጋሎ ሙዚቃ ትወዳለች።

ጓደኞቿ ለእሷ መደነስ እና ሙዚቃ መጫወት ይወዳሉ።

2

ጓደኞቿ በታክጋሎ ዊልቸር ላይ የሙዚቃ ማጫወቻ ገጠሙላት።

በዊልቸሩ በአንደኛው በኩል አንድ ቁልፍ ስትነካ ሙዚቃው መጫወት ይጀምራል።

3

ታክጋሎ እጆቿን በመዘርጋት ሙዚቃ በሚጫወተው ዊልቸር ላይ ትጨፍር ነበር።

በራሷ ዳንስ ተለማመደች እና ከዛም ከጓደኞቿ ጋር መደነስ ጀመረች።

4

አንድ ቀን ጓደኞቿ በጋዜጣ ላይ የዳንስ ውድድር ሲተዋወቅ አዩ።

ታክጋሎን ማወዳደር ይችሉ እንደሆነ የታክጋሎን እናት ጠየቋት።

የታክጋሎ እናት ተስማማች።

5

የታክጋሎ ጓደኞች ለዳንስ ውድድሩ ቪዲዮ ለመስራት የእናቷን ሞባይል ተበደሩ።

ታክጋሎ የምትወደውን ዘፈን ስትጨፍር በቪዲዮ ቀረጿት፣ ከዚያም የቪዲዮውን ወደ ውድድሩ ላኩት።

ታክጋሎም ለውድድሩ ተመረጠች።

6

የውድድሩ ቀን ደረሰ።

ታክጋሎ አዲስ የሚያምር ልብስ ለብሳለች።

ሙዚቃው ሲከፈት ግርማ ባለው ሁኔታ እና በደስታ ተንቀሳቀሰች።

7

በታዳሚው ውስጥ የነበሩት ሰዎች "ታክጋሎ! ታክጋሎ!" እያሉ ጮሁ።

እውነትም የዘመኑ የዳንስ ኮከብ ነበረች።

ታክጋሎ ውድድሩን እና ብዙ ሽልማቶችን አሸነፈች።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የታክጋሎ የሙዚቃ ተሽከርካሪ ወንበር
Author - Diana Tebeila
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration - , Diana Tebeila
Language - Amharic
Level - Longer paragraphs