ጎበዙ ኖሙሳ
Zandile Malaza

በማሶይ መንደር ኑሙሳ የምትባል በጣም ጎበዝ ልጅ ነበረች። የምትኖረው የበቆሎ ገበሬ ከነበረችው አያቷ ጋር ነው።

አብዛኞቹ የመንደሩ ሰዎች ማንበብና መጻፍ አይችሉም ነበር። ኑሮአቸውን የሚመሩት በእርሻ ነው።

1

ኖሙሳ ትምህርት መከታተል ትወድ ነበር፣ እናም አያቷ በእሷ ትኮራለች።

በየቀኑ ከትምህርት ቤት በኋላ አያቷ የቀን ተቀን የእርሻ ላይ ሥራዎችን ትሰጣት ነበር።

እህሉን ለመብላት የሚፈልጉትን ዝንጀሮዎችና ወፎች ማባረር አለባት።

2

ኖሙሳ ከሰአት በኋላ ጦጣዎችን እና ወፎችን ማሳደድ እየከበዳት መቷል። ብዙ ጊዜ የትምህርት ቤት ስራዋን ለማጠናቀቅ ጊዜ አልነበራትም።

በመንደሩ ውስጥ ያሉ ብዙ ልጆች በእርሻ ውስጥ መሥራት ስለነበረባቸው ትምህርታቸውን ሙሉ በሙሉ አቋርጠዋል።

3

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ኖሙሳ ወፎችን እና ጦጣዎችን በማሳደድ እየሰለቻት ሄደ።

"ጥሩ ሀሳብ አለኝ" ስትል አሰበች።

4

ኖሙሳ በጥንቃቄ ሁለት ረጃጅም እንጨቶችን አንድ ላይ አሰረች። በትሮቹን በስራ ልብሷ አለበሰቻቸው።

በትሮቹን ቀጥ አድርጋ ይዛ የስራዋን ኮፍያ ከላይ አስቀመጠች።

አስፈሪ ወፍ ማባረሪያ ነበር!

5

ኖሙሳ አስፈሪውን ወፍ ማባረሪያ በቆሎው መሃል ላይ አስቀመጠችው።

ኖሙሳም "ይህ አስፈሪ ወፍ ማባረሪያ የት/ቤት ስራ ስሰራ እርሻው ላይ ቦታዬን ይሸፍናል። እናም አያቴ እርሻው ላይ እንዳለሁ ታስባለች።'' ብላ ለራሷ ፈገግ አለች።

6

በየቀኑ የትምህርት ቤት ቦርሳዋን ወደ እርሻው ትወስዳለች።

የትምህርት ቤት ዩኒፎርሟን ለብሳ የስራ ልብሷን በአስፈሪው ወፍ ማባረሪያ ላይ ታስቀምጣለች።

ከዛም በዛፍ ጥላ ስር የቤት ስራዋን ትሰራለች።

7

ቀናት አለፉ፣ ኖሙሳ "አያቴ ስለ ብልህ እቅዴ በጭራሽ አታውቅም" ብላ አሰበች።

ኖሙሳ በተመሳሳይ ጊዜ ተደነቀች እናም ተገረመች።

ጦጣዎቹ እና ወፎቹ ወደ የበቆሎው መስክ አልገቡም።

8

አንድ ቀን ከሰአት በኋላ የኖሙሳ አያት አዳዲስ በቆሎችን ለመውሰድ ወደ እርሻው ሄደች።

እርሻው በጣም ጸጥ ያለ ነበር። ዝንጀሮም ሆነ ወፍ አልነበረም።

አያቷም "ኖሙሳ ጥሩ ስራ እየሰራች ነው" በማለት ለራሷ አሰበች።

9

አያቷ "ኑሙሳ! ኑሙሳ የት ነሽ?" ብላ ተጣራች።

ምንም ምላሽ አልነበረም።

ከዚያም የኖሙሳን ልብስ ለብሶ በእርሻው መካከል ያለውን አስፈሪውን ወፍ ማባረሪያ አየች።

10

አያቷ ኖሙሳ ያደረገችውን ስትገነዘብ በልጅ ልጇ ኮራች።

እሷም "ይህ በጣም ድንቅ ሃሳብ ነው። ኖሙሳ ጦጣዎችን እና ወፎችን ለማባረር ወደ ሜዳ መግባት የለበትም።'' ስትል አሰበች።

11

በመንደሩ ውስጥ ያሉት ሁሉም ሰዎች የኖሙሳን ብልህ ሀሳብ ወደዱት። ሁሉም በእርሻቸው ላይ አስፈሪ ወፍ ማባረሪያዎችን መጠቀም ጀመሩ።

አስፈሪዎቹ ወፍ ማባረሪያዎች ዝንጀሮዎችን እና ወፎችን ከእርሻ ያርቁ ነበር።

እና ልጆቹ ሰብሎችን ከመጠበቅ ይልቅ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ቻሉ።

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጎበዙ ኖሙሳ
Author - Zandile Malaza
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration -
Language - Amharic
Level - First paragraphs