

በአንድ ሞቃታማ የበጋ ቀን፣ ኮሲ ምን ማድረግ እንዳለባት እያሰበች ወዲያና ወዲህ እየተራመደ ነበር።
እናቷ ኮሲን ትታ ወደ ሜዳ ሄዳ ነበር።
"በራሴ ምን ላድርግ?" እያለች ኮሲ ለራሷ ተናገረች።
አንድ ሀሳብ በኮሲ አእምሮ ውስጥ መጣ።
"ወንዙ ላይ ልዋኝ ነው፣ ግን ማን ከእኔ ጋር ይሄዳል?" ብላ ኮሲ አሰበች።
በዚህ ጊዜ እማማ ሶፊልብስ የሞላበት ትልቅ ቅርጫት ተሸክማ ወደ ወንዙ እየሄደች ነበር።
"እማማ ሶፊን ተከትዬ ወደ ወንዙ ልሄድ ነው" አለች ኮሲ ለራሷ።
"እባክዎ ከእርስዎ ጋር ወደ ወንዙ መሄድ እችላለሁ?" በማለት ኮሲ ጠየቀች። እማማ ሶፊ ፈገግ ብላ ጭንቅላቷን ነቀነቀች።
እግረ መንገዳቸውንም ኖዚፎ ተቀላቀላቸው። ኖዚፎ መዋኘት ፈጽሞ አይወድም ነገር ግን ሌሎች ሲዋኙ ማየት ያስደስትው ነበር።
ወንዙ ላይ፣ ኮሲ በልቧ፣ "ዛሬ ጥልቀት በሌለው ውሃ ውስጥ፣ እንደ ህፃን ልጅ እዋኛለሁ ! ጥልቅ ውሃ ውስጥም መዋኘት እንደምችል ለሁሉም አሳያለሁ።" ብላ ወደ ወንዙ ገባች። ውሃው ተደበላለቀ!
ኖዚፎ ከቅርብ ርቀት እየተመለከተች ነበር።
ኖዚፎ ስትመለከት ሁሉም ልጆች በወንዙ ውስጥ እየተዝናኑ ነበር።
በጫጫታ ይዋኙ ነበር።
በውሃው ውስጥ በደስታ ይጯጯሃሉ።
ኖዚፎ እንደገና በጥንቃቄ ተመለከተች፣ የሆነ ነገር የተለየ ይመስላል። ኮሲ ከሌሎቹ ልጆች ርቃ ትዋኝ ነበር። ኖዚፎ ጠጋ ብላ እንደገና ተመለከተች።
ባየችው ነገር ፈርታ በወንዙ ዳር ልብስ ወደ ሚያጥቡት ሴቶች ሮጠች።
ኖዚፎ "እርዱኝ! ኮሲ እየሰጠመች ነው" ብላ ጮኸች።
በቅጽበት እማማ ሶፊ ወደ ውሃው ውስጥ ዘለለች። በወንዙ ቁልቁል ዋኘች።
ኮሲን ፍለጋ ከውሃው በታች፣ ከዛ ወደ ላይ፣ ከዛም እንደገና ስር ዋኘች።
ኮሲን ክንዷን ይዛ ጥልቀት ወደ ሌለው ውሃ ዋኘች። ከዚያም እማማ ሶፊያ ኮሲን ተሸክማ ከወንዙ አወጣቻት።
እማማ ሶፊ በዋይታ የሚጮኹትን ህጻናት እና ሴቶችን በፍጥነት አለፈች።
ወደ መንደሩ ክሊኒክ በፍጥነት ኮሲን በጀርባዋ ይዛ ስትሄድ ኖዚፎ ከኋላዋ ሮጠች።
በክሊኒኩ ማማ ለመርዳት የመጣችዉን ነርስ ኖክሶሎን አገኘቻት።
ነርስ ኖክሶሎ በፍጥነት ኮሲን ወደ ክፍሉ ወሰደቻት እናም ሌሎች ነርሶች ለመርዳት ተሯሯጡ።
"ደህና ናት! ለደቂቃ ያህል በውሃ ውስጥ ስላልነበረች እድለኞች ነን!" አለች ነርስ ኖክሶሎ።
እማማ ሶፊ ትልቅ እፎይታ ተነፈሰች።
ክሊኒኩ ውስጥ የነበሩት ሁሉ በጀግንነቷ እና በዋና ችሎታዋ አደነቋት።
እማማ ሶፊም በትሕትና "ሕይወትን ማዳን በመቻሌ አመስጋኝ ነኝ።" አለች።
ዜናው ለአካባቢው አለቃ ደረሰ። እማማ ሶፊን እንድትጠራ መልእክተኛ ላከች።
እማማ ሶፊ እንዴት ጎበዝ ዋናተኛ እንደሆነች ለአለቃዋ ገለጸች።
"ጓደኛዬ ልጅ እያለሁ በወንዙ ማዶ ይኖር ነበር ። ውሃ የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አካል ነበር ፣ መዋኘት መማር ነበረብን!" አለች።
አለቃዋ ስብሰባ ጠርታ ለእማማ ሶፊ በጀግንነት ስራዋ ሽልማት እንደምትሰጣት አሳወቀች።
ሴቶች በልልታ፣ ወንዶች በፉጨት፣ ልጆች በደስታ ጮኹ። ከዚያን ቀን ጀምሮ ልጆች እማማ ሶፊን "ምንም የሚነካኝ የለም፣ ደፋሯ እናት ሶፊ ከጎኔ!" እያሉ እየዘፈኑ ይከተሏት ጀመር።


