የማቶድዚ ደግነት
Tshedza Tlhako

በአንድ ወቅት ማቶድዚ የምትባል ልጅ ነበረች።

ማቶድዚ ከእናቷ እና ከአያቷ ጋር በአንድ መንደር ውስጥ ትኖራለች።

1

አንድ ቀን፣ የማቶድዚ እናት በሌላ መንደር ለምትኖረው አክስቷ መልእክት እንድትወስድ ጠየቀቻት።

"ብዙውን ጊዜ የምንጠቀመውን መንገድ ተከተይ" እናቷ ማቶድዚን አስታወሰቻት።

2

ማቶዲዚ ወደ አክስቷ ቤት የሚወስደውን የተለመደ መንገድ ተከትላ መልእክቱን አደረሰች።

ወደ ቤት እየሄደች ሳለ በአቅራቢያዋ "እባካችሁ እርዱኝ" የሚል ድክም ያለ ድምፅ ሰማች።

3

ማቶድዚ ዙሪያውን ተመለከተች እና አንዲት ሴት በመንገድ ላይ ተኝታ አየች።

ሴትየዋን ሰላም ብላ፣ "ለምን እዚህ ተኛሽ ?" ብላ ጠየቀቻት።

4

ሴትየዋም "ደካማ ነኝ ፣ ታምሜያለሁ እናም ከቤቴ በጣም ርቄያለሁ" ስትል መለሰች።

ማቶድዚ ለሴትየዋ አዘነችላት።

5

ሴቲቱንም፣ "ወደ ቤቴ እወስድሻለሁ ምክንያቱም ቅርብ ነው" አለቻት።

ማቶድዚ ሴትየዋን እንድትነሳ ረዳቻት። እስኪደርሱም ድረስ በጣም በዝግታ ተጓዙ።

6

ማቶድዚ ፣ እናቷ እና አያቷ ሴትዮዋን ደህና እስክትሆን ድረስ ይንከባከቧት ነበር።

7

ሴትዮዋም እሷን ስለተንከባከቧት በጣም አመስጋኝ ነበረች።

ማቶድዚንም ደፋር እና ተንከባካቢ በመሆኗ አሞካሽታታለች።

8

ሴትየዋ ለማቶዚ እና ለቤተሰቧ እንዲህ አለቻቸው "ያደረጋችሁልኝን ፈጽሞ አልረሳውም''

ሶስት ቀናት ካለፉ በኋላ ሁለት ምኞቶችን እንድትመኙ እፈልጋለሁ።

9

ከሶስት ቀናት በኋላ ማቶድዚ ፣ እናቷ እና አያቷ ሁለት ምኞቶችን ተመኙ።

የመጀመሪያ ምኞታቸው ቆንጆ ቤት እንዲኖራቸው ነበር።

10

ሁለተኛው ምኞታቸው እንጨት ለመሰብሰብ ሩቅ እንዳይሄዱ ከቤቱ አጠገብ ጫካ እንዲኖራቸው ነበር።

ሴትዮዋ እንደተናገረችው ሁለቱም ምኞታቸው ተፈፀመ።

11

ማቶድዚ እና ቤተሰቧ ከጫካው አጠገብ ባለው ውብ ቤታቸው ውስጥ በደስታ ኖሩ።

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የማቶድዚ ደግነት
Author - Tshedza Tlhako
Translation - Tesfamichael Hailu
Illustration -
Language - Amharic
Level - First paragraphs