

ድመት እና ውሻ ጥሩ ጓደኞች ናቸው.
ጓደኛቸውን ዶሮን በልደቱ ቀን ለመጎብኘት ወሰኑ።
ዶሮ በሌላ መንደር ይኖር ስለ ነበር። ድመት እና ውሻ እዛ ለመድረስ ሁለት ቀናትን ይወስድባቸው ነበር።
ድመቷ እና ውሻው የተለያየ ባህሪ አላቸው።
ውሻው መብላት እና መተኛት ይወድ ነበር እና አንዳንድ ጊዜ ተንኮለኛ ነበር።
ድመቷ ደግ፣ ለጋስ እና ሊታመንባት የምትችል ነበረች።
ጉዟቸውን ለማቀድ በውሻው ቤት ተገናኙ።
ውሻው "ለመጀመሪያው ቀን ምግብ እኔ አመጣለሁ" ሲል አቀረበ።
ድመትም "ለሁለተኛው ቀን ደሞ እኔ አመጣለሁ" አለች።
እንዳይረሱት ሁሉንም ነገር ጻፉ።
"ጓደኛችንን ካየን ጥቂት ጊዜ አልፎናል እናም በቅርቡ ዶሮን ልናየው መሆኑ አስደሳች ነው።" አለ ውሻ ድመትን ወደ ቤቷ እየሸኛት።
ድመቷም ውሻውን "ወደ ቤት ስላካሄድከኝ አመሰግናለሁ" አለችው።
በማግስቱ በጣም በማለዳ ጉዞአቸውን ለመጀመር ተገናኙ።
በመንገድ ላይ በደስታ እየዘፈኑ እና እየጨፈሩ ነበር።
ከጥቂት ቆይታ በኋላ በአንድ ትልቅ ዛፍ ስር አረፉ። "እርቦኛል! እንብላ" አለች ድመት።
ውሻ በችኮላ በሁለት ሳህኖች ምግብ ሞላ። ምግቡ ዘይትና ውሃ የሞላበት ነበር።
ድመት፣ "ይህ ለሁለታችን ያመጣኸው ምግብ ነው?" ብላ ጠየቀች።
ድመት ጓደኛዋ የተስማሙበትን ምግብ ስላላመጣ ተናደደች። የውሻን ምግብ አትበላም።
"ለምንድን ነው እየጠበቅሽ ያለሽው?" ውሻ ጠየቀ። ድመት ቅሬታዋን ትታ እንደምትበላ ተስፋ አደረገ።
የተበሳጨችው ድመት፣ "ለምን አንተ ብቻ የምትፈልገውን ምግብ አመጣህ?" ብላ ጠየቀች።
ውሻው በፍጥነት እየበላ ስለነበር ሳህኑ ተንሸራተተ።
ሁሉም የውሻ ምግብ መሬት ላይ ፈሰሰ።
"ጓደኛዬን አትጨነቅ" አለች ድመት።
ድመት በጣም ቆንጆ የሆኑትን ሳንድዊቾች አወጣች። መብላት ጀመረች።
ውሻው የድመቷን ምግብ አየና ለመብላት ጓጓ።
ድመት በልታ እንደጨረሰች፣ እቃውን ሰብስባ ውሻን "ጉዟችንን መቀጠል እንችላለን?" አለችው።
ስለቀጣዩ ጉዞ ምንም አላወሩም። የውሻ ሆድ በረሃብ የጮህ ነበር።
በዚያ ምሽት ድመት ለራሷ ምግብ አዘጋጀች። በቂ ምግብ በማምጣቷ ደስተኛ ሆና ተኛች።
ውሻ ተርቦ ተኛ።
ጠዋት ላይ ድመት ለራሷ ትንሽ ቁርስ አቀረበች። ውሻ የድመቷን ምግብ መመልከቱን ማቆም አልቻለም።
ድመቷም ለውሻው ጥቂት ምግብ አቀረበች።
ውሻ "ይቅር በይኝ በጣም ራስ ወዳድ ነበርኩ" አለ።
ድመቷ "አብረን እንብላ" ብላ መለሰች።
ለመብላት ተቀመጡ።
ጉዟቸውን ሲቀጥሉ እንደገና ጓደኛሞች ሆኑ።
በጊዜ ዶሮ ቤት ደረሱ።
"ጓደኞቼ ጉዟችሁ እንዴት ነበር?" ዶሮ ጠየቀ።
ድመት እና ውሻ እርስ በእርሳቸው ፈገግ እያሉ "በጣም ጥሩ ነበር" ብለው መለሱ።
በእርግጥም ታላቅ የልደት ድግስ ነበር።
በሉ፣ ዘፈኑ፣ ጨፈሩ።


