የቦህላሌ ጀብዱ
Gianna Ambrosano
Gianna Ambrosano

ሰላም፣ ስለተዋወቅን ደስ ብሎኛል!

ስሜ ቦህላሌ ነው።

ዘጠኝ ዓመቴ ነው።

እድሜዎ ስንት ነው?

1

ይህ የኔ ቤተሰብ ነው። እኔ ታናሽ ስሆን አያቴ ከሁሉም ትልቋ ነች።

አንድ ወንድም አለኝ፡፡ ሁለት ዓመት ይበልጠኛል። እህትም አለችኝ፡፡ እሷ ወንድሜን ሦስት ዓመት ትበልጠዋለች።

የወንድሜ እና የእህቴ ዕድሜ ስንት ነው?

2

ወንድሜና እህቴ ወደ ተራራው ሄደው ፍራፍሬ እንዲሰበስቡና እና ወደ ወንዝ እንዲሄዱ ተፈቅዶላቸዋል።

እኔም እነዚያን ነገሮች ባደርግ ደስ ይለኛል። እኔ በጣም ልጅ፣ በጣም ትንሽ፣ በጣም ደካማ እንደሆንኩና በቂ ድፍረት እንደሌለኝ ሁሉም ሰው ሁልጊዜ ይነግረኛል።

3

ቤተሰቦቼ ባመኑኝ ብዬ እመኛለሁ!

አያቴ ወደ ክፍሌ ትገባለች። ትስመኝና ‹‹ደህና እደሪ›› ትለኛለች።

ከዚያም በጆሮዬ ‹‹በአንቺ እንደምተማመን ሁልጊዜ አስታውሺ›› በማለት ሹክ ትለኛለች፡፡

4

እንቅልፍ ይወስደኛል፡፡ በሕልሜ በጠርሙስ ውስጥ መልዕክት አገኛለሁ፡፡ መልዕክቱም ይህ ነው፡-

‹‹ደፋር መሆን ከፈለግሽ በካርታውን ላይ ወደተመለከተው ወደ ከፍተኛው ተራራ ሂጂ። እዚያም ልዩ መጠጥ ታገኛለሽ።

ያን መጠጥ አንድ ጊዜ መጠጣት በዓለም ላይ በጣም ደፋሯ ሴት ልጅ ያደርግሻል።››

ያን መጠጥ አንድ ጊዜ መጠጣት በዓለም ላይ በጣም ደፋሯ ሴት ልጅ ያደርግሻል።››

5

እንደ አያቴ ብልህ አይደለሁም። እንደ ወንድሜ ጠንካራ አይደለሁም፤ እንደ እህቴም ደፋር አይደለሁም።

ነገር ግን ይህን መጠጥ ካገኘሁ ማንኛውንም ነገር ማድረግ እችላለሁ፡፡

ካርታውን እንድከተል እርዱኝ፣ ወደ ፊት 50 እርምጃዎችን ቁጠሩ።

1፣ 2፣ 3፣

6

47, 48, 49, 50 ደረጃዎች!

እንዴ አላምንም፣ ወንዝ! ወደ ሌላኛው ወገን እንዴት እደርሳለለሁ? መዋኘት ስለማልችል እተወዋለሁ ብዬ አስባለሁ።

በዉኃሃው ላይ የሚንሳፈፈውን ቅጠል ተመልከቱ!

ሀሳብ መጣልኝ።

7

መንሳፈፊያ መስራት እችላለሁ!

አምስት የዛፍ ቅርንጫፎች እሉኝ፡፡ ከአስራ አንድ ቅርንጫፎች መንሳፈፊያ ለመስራት ስንት ተጨማሪ ቅርንጫፎች ያስፈልጉኛል?

መንሳፈፊያውን ከሰራሁ በኋላ ያለ ዋና ወንዙን መሻገር እችላለሁ። ቀጥሎ ወዴት እሄዳለሁ?

8

ከ100 እርምጃዎች በኋላ የጠፋሁ ይመስለኛል! ተራራው የት ነው?

ወደ ከፍተኛው ተራራ የሚወስደውን መንገድ በጭራሽ አላገኘውም። በጣም ትንሽ ልጅ ስለሆንኩ መተው እንዳለብኝ አስባለሁ፡፡

9

ቀጭኔው በጣም ረጅም ስለሆነ ተራራውን ማየት ይችላል።

ይህን ዛፍ ከወጣሁ እንደ ቀጭኔ እረዝማለሁ!

ተራራው ምን ያህል እንደሚርቅ አያለሁ።

10

ከዛፉ ላይ እወርዳለሁ፡፡

ከ200 ደረጃዎች በኋላ እኔ በትልቁ ተራራ ስር ነኝ።

የሚያስፈሩ ዓይኖች ከዋሻ ውስጥ ሆነው ያዩኛል!

ስለፈራሁ እተወዋለሁ ብዬ እሰጋለሁ።

11

እንደገና በጥንቃቄ ተመልከቱ፣ እነዚያ አስፈሪ ዓይኖች የጢንዚዛ ዓይኖች ናቸው።

ጢንዚዞቹ በዋሻው በኩል ወደ ተራራው ጫፍ ስሄድ ሊመሩኝ ይችላሉ።

12

እነሆ እኔ በተራራው አናት ላይ ነኝ!

በድምሩ ስንት ደረጃዎች ተጓዝኩ?

የጀግንነት ልዩ መጠጤን አየሁት! አሁን ልጠጣው ነው።

13

‹‹ደህና አደ.......ርሽ!›› አለችኝ አያቴ።

በድንገት እነቃለሁ!

‹‹አያቴ፣ ህልም አየሁ፡፡›› ‹‹ስለ መልዕክቱ እና ስለ ጉዞዬ ለአያቴ እነግራታለሁ።››

‹‹እኔ አሁንም እንዳንቺ ጥበበኛ አይደለሁም። አሁንም እንደ ወንድሜ ጠንካራ ወይም እንደ እህቴ ደፋር አይደለሁም።››

14

አያቴ ፈገግ አለችና ‹‹ደፋር እንዳልሆንሽ እየነገርሽኝ ነው? ወደ ትልቁ ተራራ እንዴት ደረስሽ? በዋሻው ውስጥ እንዴት አለፍሽ?

ልዩ መጠጥ አያስፈልሽም፣ ምክንያቱም ደፋር ስለሆንሽ!››

15

ጥያቄዎች

1. ቦህላሌ ስንት ወንድሞችና እህቶች አሏት?
2. በሕልሟ ውስጥ ባየችው ጠርሙስ ውስጥ ምን አለ?
3. ወንዙን እንዴት ተሻገረች?
4. ዛፍ የመውጣት ሀሳብ የሰጣት የትኛው እንስሳ ነው?
5. በዋሻው ውስጥ ምን አየች?
6. ከተራራው አናት ላይ ምን አገኘች?

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የቦህላሌ ጀብዱ
Author - Gianna Ambrosano, Laila Wermelinger, Selina Buschor
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Gianna Ambrosano, Laila Wermelinger, Selina Buschor
Language - Amharic
Level - Longer paragraphs