እ! እግርኳስ
Stella Kihweo
Onesmus Kakungi

ከጓደኛዬ ከቹማ ጋር መጫወት እወዳለሁ።

1

ጥሩ ጓደኞች ነን።

አንዳችን ወደ አንድ ቦታ ስንላክ አብረን እንሄዳለን።

2

አንድ ቀን፣ አያቴ ጨውና የምግብ ዘይት እንድገዛ ወደ ሱቅ ላከችኝ።

ከቹማ ጋር ሄድኩ።

3

በመንገድ ላይ ጓደኞቻችን እግር ኳስ ሲጫወቱ አየን።

4

‹‹እ! እግር ኳስ!›› አልኩ፡፡

እኔም ለመጫወት ፈለግሁ።

5

ቹማን ‹‹ከእነሱ ጋር መጫወት እንችል እንደሆነ እንጠይቅ፡፡ እግር ኳስ መጫወት በጣም እወዳለሁ›› አልኩት።

6

ቹማ ‹‹መጀመሪያ ወደ ሱቅ እንሂድ፣ ከዚያ ለመጫወት መምጣት እንችላለን›› በማለት መለሰ።

7

እኔ ግን ‹‹ቆይ በመጀመሪያ እንጫወት! አያቴ እንድንመለስ አትፈቅድልንም›› አልኩት።

8

ለመጫወት ጓደኞቻችንን ተቀላቀልን። እኔ ግብ ጠባቂ ሆንኩ።

ጎሎቹ ከሁለት ትላልቅ ድንጋዮች የተሠሩ ነበሩ፡፡

9

ኳሷን ለመያዝ ተጣጣርኩ።

ጓደኞቼ ምንም ግብ ማስቆጠር አልቻሉም።

10

ሜዳው በአሸዋ እስኪሞላ ድረስ ተጫወትን።

11

ከዚያም ወደ ሱቅ ሄድን፡፡ የአያቴ ገንዘብ ጠፍቷል! ማልቀስ ጀመርኩ።

ቹማ ‹‹ማልቀስ አቁም መጀመሪያ መጫወት ፈልገህ ነበር›› ብሎ ጮኸብኝ።

12

ጨው ወይም የምግብ ዘይት ሳንይዝ ወደ ቤታችን ተመለስን።

በጣም ቆሽሸንና ተጨንቀን ነበር።

13

ቤት ስንደርስ አያት ተናደደች።

መጀመሪያ የጠየቀችን ጥያቄ ‹‹ይህን ሁሉ ጊዜ የት ነበራችሁ?›› የሚል ነበር፡፡

14

እውነቱን መናገር ነበረብን።

‹‹ያለ ፍቃድ በጭራሽ ለመጫወት መሄድ የለባችሁም›› ስትል አስጠንቀቀችን።

15

ዳክዬዎችን ለመመገብ ሄድን፡፡

በኋላ ራሳችንን አጸዳን።

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
እ! እግርኳስ
Author - Stella Kihweo
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Onesmus Kakungi
Language - Amharic
Level - First sentences