የሚያወራው ቦርሳ
Caroline Lentupuru
Wiehan de Jager

በአንድ ወቅት አንዲት ግዙፍ ሴትዮ ነበረች። ከዕለታት አንድ ቀን በሐይቁ አጠገብ የእግር ጉዞ ስታደርግ ነበር።

ሦስት ትናንሽ ሴቶች ልጆችን አግኝታ ‹‹ከእናንተ መካከል በሁለቱም ወላጆቹ የሚወደድ ማነው?›› ብላ ጠየቀቻቸው።

1

ከልጆቹ አንዷ ‹‹እናቴ የበለጠ ትወደኛለች›› አለች።

ሌላዋ ‹‹አባቴ የበለጠ ይወደኛል›› አለች።

ሦስተኛዋ ግን ‹‹በሁለቱም ወላጆቼ እወደዳለሁ›› አለች፡፡

2

ግዙፏ ሴትዮ በሁለቱም ወላጆቿ የምትወደደውን ልጅ የማገዶ እንጨት በመሸከም እንድትረዳት ጠየቀቻት።

ልጅቷ ግዙፏን ተከተለቻት።

3

የተወሰነ ርቀት ተጓዙ። ልጅቷ ግዙፏን ሴትዮ ‹‹የማገዶ እንጨትሽ የት ነው?›› በማለት ጠየቀቻት፡፡

ግዙፏም ‹‹እዚያ እዛፎቹ አጠገብ ነው!›› ስትል መለሰች፡፡

4

ዛፎቹ አጠገብ ሲደርሱ ልጅቷ እንደገና ‹‹የማገዶ እንጨትሽ የት ነው?›› አለቻች፡፡

ግዙፏም ‹‹አሁን እንኳን ሩቅ አይደለም!›› ስትል መለሰች፡፡

5

በመንገድ ላይ አንድ ሰው አገኙ። እሱም ግዙፏን ‹‹የልጅሽ ስም ማን ነው?›› በማለት ጠየቃት፡፡

ግዙፏም ‹‹የምታወራው ቦርሳ ትባላለች›› ስትል መለሰችለት።

6

ልጅቷ እየፈነደቀች ዘፈነች፡-

የምታወራ ቦርሳ አይደለሁም።
ስሜ ካሙንጌ ነው!
ኦ! የምወዳት እናቴ።
ኦ! የምወደው አባቴ።
ኦ! ወተት ለመጠጣት የምጠቀምበት ቅል!

7

ሰውየው ልጅቷ የዘፈነችውን ሲሰማ ከሴትዮዋ ነጥቆ አዳናትና ወደ ወላጆቿ ወሰዳት።

ታሪኩ በዚህ አበቃ!

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የሚያወራው ቦርሳ
Author - Caroline Lentupuru
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Wiehan de Jager
Language - Amharic
Level - Longer paragraphs