አዱን ቆንጆዋ
Taiwo Ẹhinẹni
Wiehan de Jager

አዱን በጣም ቆንጆ ነበረች። በመንደሯ ያሉ ወንዶች ሁሉ ሊያገቧት ይፈልጉ ነበር።

አዱን ግን ሁሉንም እምቢ አለች።

1

በአንድ የገበያ ቀን አንድ ሰው እግር ከአንድ ሰው፣ ክንድ ከሌላና አካሉን ደግሞ ከሦስተኛው ሰው ተዋሰ።

ከዚያም ይህ ሰው ሁሉንም ክፍሎች አንድ ላይ አቀናጃቸው፡፡ አንገቱን ከላይ አድርጎ ወደ ገበያ ሄደ።

2

ይህ ሰው አዱንን ስለፈለጋት ሊያገባት ቆርጦ ነበር። አዱንም በመልኩ ተማረከች። ከእሱ ጋር መሆንንም ፈለገች፡፡

ሰውዬው የመጣው ከሩቅ ከተማ ነበር፤ አዱንም ከእርሱ ጋር ለመመለስ ወሰነች፡፡

3

አዱንና ሰውዬው ወደ ቤት ሲሄዱ የእግሮቹ ባለቤት እግሮቹን ወሰደበት። ከዚያም የክርኖቹ ባለቤት ክርኖቹን መልሶ ወሰደበት፡፡

እና በመጨረሻም የአካሉ ባለቤት ያንን አካል መልሶ ወሰደበት፡፡

4

ጭንቅላቱ ብቻ ቀረ፡፡ እናም ጭንቅላቱ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ አዱን ፈራች፤ ቢሆንም ግን አልሸሸችም።

ከጭንቅላቱ ቤትም ደረሱ።

5

በማግስቱ ጠዋት፣ ጭንቅላቱ ወደ እርሻው ከመሄዱ በፊት ለኤሊ አንድ ነገር ነገረው። ‹‹አዱን ለማምለጥ ከሞከረች፣ ይህን ጡሩምባ በመንፋት አሳውቀኝ›› አለ ጭንቅላት።

6

ጭንቅላቱ ከሄደ በኋላ አዱን እቃዎቿን አዘጋጀች። ከዚያም መሸሽ ጀመረች።

7

አዱን መነሳቷን ሲያይ፣ ኤሊ ጡሩምባውን ነፋው፡፡ ‹‹ጭንቅላት፣ ጭንቅላት፣ አዱን ልትሸሽ ነው›› በማለት ተጣራ።

8

ጭንቅላቱ ወደ አዱን ሄደና ‹‹ወዴት ልትሄጂ ነው?›› አላት፡፡

አዱን ወደ ጭንቅላት ቤት ተመለሰች።

9

በመጨረሻ አዱን ምን ማድረግ እንዳለባት አንድ አዋቂ አማከረች።

አዋቂውም ‹‹ሂጂና የባቄላ ቂጣ ግዢ፣ በዘንባባ ዘይት ነክረሽ በዔሊ ጡሩምባ ውስጥ አስቀምጪው›› ብለው መከሯት።

10

አዱን የአዋቂውን መመሪያ ተከተለች። በቅባት የወዙትን ኬኮች በጡሩምባው ውስጥ ከተተቻቸው።

11

አዱን በማግስቱ እቃዋን ይዛ እንደገና መሸሽ ጀመረች።

ኤሊ ጡሩንባውን ሊነፋ ሲያነሣ ጣፋጮቹ የባቄላ ኬኮች ወደ አፉ ገቡ።

12

ዔሊ እስኪበቃው በላ፡፡
አዱንም አመለጠች፡፡

13
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አዱን ቆንጆዋ
Author - Taiwo Ẹhinẹni
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Wiehan de Jager
Language - Amharic
Level - First paragraphs