ቦቢ ወደቀ
Salome Ledwaba
Martin Letsoalo

ይህ የኔ ውሻ ነው። ስሙ ቦቢ ነው።

አዳኝ ውሻ ነው።

1

ቦቢ ትናንሽ እንስሳትን ማደን ይወዳል.

በረዥም ሣር ውስጥ መጫወትም ይወዳል።

2

አንድ ቅዳሜ ቦቢ ለአደን ብቻውን ወጣ።

አንዲት ጥንቸል በድንጋይ ላይ አየ፡፡

ቦቢ መጎምዠት ጀመረ።

3

ጥንቸሏ ቦቢ ሲመለከታት አየችው።

ጥንቸሏ በጣም በፍጥነት ሸሸች።

4

ቦቢ ጥንቸሏን ተከትሎ ሮጠ።

ጥንቸሏን ስለመብላት ብቻ ያስብ ጀመር፡፡

ከፊት ለፊቱ የነበረውን ትልቅ ጉድጓድ አላየውም፡፡

5

ቦቢ ወደ ጥልቁ ጉድጓድ ወደቀ።

ጥንቸሏ በቀዳዳው ዙሪያ ደጋግማ ትሮጥ ጀመር፡፡

6

እንደ እድል ሆኖ፣ ሁለት ልጆች ቦቢን ሲጮህ ሰሙት፣ "ዉፍ! ዋፍ! ሱፍ!"

እሱን ለመርዳትም ወደ ትልቁ ጉድጓድ ሮጡ።

7

"በጣም ከባድ ነው!" አሉ ልጆቹ!

ቢሆንም ግን ቦቢን ከጉድጓዱ ውስጥ ማውጣት ቻሉ።

ቦኒ በጣም ደስተኛ ሆነ!

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ቦቢ ወደቀ
Author - Salome Ledwaba
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Martin Letsoalo
Language - Amharic
Level - First sentences