ባለ ትልቅ ራሱ ጉንዳንና ሰነፏ እርግብ
Terkule Aorabee
Joe Werna

ባለ ትልቅ ጭንቅላቱ ጉንዳን ጥሩ ገበሬ ነበር።

ከቤተሰቡ ጋር በመሬት ውስጥ ይኖር ነበር፡፡

1

በእርሻቸው ላይ በጣም ጠንክረው ይሰራሉ፡፡

የጉንዳን ቤተሰብ በጥሩ ሁኔታ ይኖሩ ነበር።

2

እርግብ የጉንዳን ጎረቤት ነበረች።

እርግብ ከቤተሰቦቿ ጋር በዛፍ ላይ ትኖር ነበር፡፡

3

እርግብና ቤተሰቧ አያርሱም ነበር።

ቀኑን ሙሉ ያርፋሉ።

4

እርግብ እና ቤተሰቧ በጣም ጥሩ ዘፋኞች ነበሩ።

5

"ምግብህን አካፍለን?" ስትል እርግብ ጉንዳንን ጠየቀችው።

"አይ! ሂጂና እረሺ!" ሲል መለሰ ጉንዳን።

6

እርግብ ወደ ታች በረረችና "ጉንዳን ንጉሥ ነው!" በማለት ትዘምር ጀመር፡፡

7

"ጉንዳን ንጉሥ ነው! ጉንዳን ንጉሥ ነው! ጉንዳን ንጉሥ ነው!"

ጉንዳን ይህን ዘፈን ወደደው።

8

ከበሉ በኋላ እርግብ እና ቤተሰቧ ወደ ዛፋቸው በረሩ።

9

በማግስቱ እርግብ ጉንዳን ላይ ተሳለቀች።

"ንጉሦች ትልቅ ጭንቅላት አላቸው እንዴ?" ብላ ሳቀችበት።

10

"አንቺ የማታመሰግኝና ሰነፍ ነሽ!" ስትል ጉንዳን አጉረመረመች።

11

"አዝናለሁ!" አለች እርግብ፡፡ ቀጥላም "ጉንዳን ንጉሥ ነው!" ስትል ዘፈነች፡፡

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ባለ ትልቅ ራሱ ጉንዳንና ሰነፏ እርግብ
Author - Terkule Aorabee
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Joe Werna
Language - Amharic
Level - First words