

ፍየል የእንስሳትና የአእዋፍ ንጉሥ ነበር።
ከዕለታት አንድ ቀን ስብሰባ ጠራ።
ፍየል ህልም እንዳየ ነገራቸው።
ሁሉም በጥሞና አዳመጡት።
ሕልሙ ስለ ረሃብ ነበር።
‹‹ምን እናድርግ?›› ስትል ድመት ጠየቀች ።
ዶሮ እና ዳክዬ ‹‹ንጉሡ መደብር ውስጥ ምግብ እናስቀምጥ›› አሉ።
ንጉሡ ፍየል ‹‹የማይታዘዝን ሁሉ እሰሩ›› አለ።
አዲስ ንጉሥ ለመምረጥ ጊዜው ነበር፡፡
ድመትን መርጠዋል፡፡
ፍየል ድመት ንጉሥ እንድትሆን አልፈለገም፡፡ ‹‹እኔ ነኝ ንጉሡ፡፡››
ፍየል ምግብ አልበላም፡፡
ላም ‹‹ምን እናድርግ?›› ስትል ጠየቀች፡፡
እንስሳትና አእዋፍ በአንድነት ተነጋገሩ።
በፍየል ተናደዱበት።
ውሻ ‹‹ንጉሥ በነበረበት ጊዜ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ነበርኩ›› አለ።
በግ ‹‹ያማረውን የበግ ፀጉር ለልጆቹ ሰጠኋቸው›› አለ።
አሳማም ‹‹ንጉሥ በነበረ ጊዜ የአትክልት ስፍራውን እጠብቅ ነበር›› ሲል ጮኸ፡፡
<<ፍየል ለዘላለም ንጉሥ እንደሚሆን አስቦ ነበር?>> በማለት ጠየቀ በግ።
ፍየል ለንጉሥ ድመት ምግብ እንዲወስድ እንስሳቱ ተስማሙ።
እንስሳቱ ፍየልን አገኙት። ፍየል ‹‹ሁልጊዜ ንጉሥ እሆናለሁ›› አለ፡፡
‹‹አስረን ወደ አዲሱ ንጉሥ እንወስድሃለን።››
ላም ፍየልን ወደ ንጉሡ አደባባይ ወሰደችው፡፡
ሌሎችም በደስታ ፈነጠዙ።
ለዚህም ነው ፍየሎች በሚጎተቱበት ጊዜ ለመንቀሳቀስ የሚያስቸግሩት፡፡

