ገበያ ውስጥ እንዴት እንደጠፋሁ
Timothy Kabare
Catherine Groenewald

የኔ መንደር ፍየሎች አሉት።

ከትላልቅ ከተሞች በጣም የራቀ ነው፡፡

1

እናቴ ‹‹ኤሊ፣ ለስድስተኛ ዓመት ልደትህ ስጦታ አለን›› አለችኝ።

2

እናቴ፣ አክስቴ እና እኔ አውቶቡሱን ጠበቅን፡፡

3

እኔ እናቴ ጭን ላይ ተቀመጥኩ፡፡

ቀኑን ሙሉ ተኛሁ፡፡

4

ገበያ ደረስን፡፡

ቆንጆ ሰማያዊ ሄሊኮፕተር አየሁ፡፡

5

አንድ መደብር ፍራፍሬ አለው፡፡

እናቴን ‹‹እነዚህ የትኞቹ ናቸው?›› አልኳት፡፡

6

እናቴ ‹‹እነዚህ ፖሞች ናቸው›› አለችኝ፡፡

‹‹እባክሽ አንድ ፖም ግዢልኝ›› በማለት ለመንኳት፡፡

7

የእናቴን እጅ እረስቼው ነበር፡፡

ስለ ፖሙ ብቻ ሳስብ ነበር፡፡

8

በልቼ ስጨርስ ብቻዬን ነበርኩ።

ማልቀስ ጀመርኩ።

9

አንዲት ሴት ሌሎች ልጆች ወዳሉበት ወሰደችኝ።

10

ልጆች በገበያው የሚሸጡ መሰለኝ።

ከበፊቱ የበለጠ አለቀስኩ።

11

አንድ ሰውዬ ‹‹ኤሊ የት ነው?›› ሲል ጠየቀ፡፡

እኔም ከሱ ተደበቅሁ፡፡

12

የማውቀው የእናቴ ድምፅ ‹‹ኤሊ!›› ሲል ሰማሁ፡፡

በጣም ደስተኛ ነበርኩ፡፡

13

አክስቴ የሚያምር ሄሊኮፕተር አወጣች።

‹‹ያንተ ነው!›› አለችኝ፡፡

14
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ገበያ ውስጥ እንዴት እንደጠፋሁ
Author - Timothy Kabare, Ursula Nafula
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Catherine Groenewald
Language - Amharic
Level - First words