

ኤብላ የምትባል ልጅ ነበረች። የወር አበባዋ ከመጣ ለማግባት እንደምትገደድ ስለምታውቅ እንዳይመጣ አላህን ትለምነዋለች።
ኤብላ ማግባት አልፈለገችም። እንደውም የወንድሟን ደብተሮች ማንበብ ትወድ ነበር!
የወር አበባዋ በመጣ ጊዜ እያለቀሰች መምጣቱን ከአባቷ ለመደበቅ ሞከረች። አባቷ ግን መምጣቱን ደረሰበት። ኤብላን ማግባት የሚፈልግ አንድ ሀብታም ሰው ስለነበር አባቷ ደስተኛ ነበር።
‹‹እባክህ በልጅነቴ ወደ ባል ቤት እንዳትልከኝ›› ስትል ኤብላ ለመነችው። አባቷ ግን በሃሳቧ አልተስማማም።
ከማግባት ውጪ ምን ማድረግ እንደምትፈልግ ጠየቃት። እንደ ወንድሟ ኢብራሂም መማር እንደምትፈልግ ነገረችው። አባቷ ሳቀባት።
‹‹ትምህርት ምን ያደርግልሻል?›› በማለት ጠየቃት።
‹‹ባባ፣ የኢብራን ማስታወሻ ማንበብ እወዳለሁ፡፡ እና እኔም ትምህርት ቤት እንድገባ ከፈቀድክልኝ ጎበዝ እንደምሆን እርግጠኛ ነኝ።››
‹‹ትምህርት ግን ምን ይጠቅምሻል?›› ሲል ጠየቃት።
‹‹ታዲያ ኢብራሂምስ ለምንድነው የሚማረው?››
‹‹እሱ ወንድ ነው!››
‹‹አባ፣ እኔስ ያንተ ልጅ አይደለሁም?››
‹‹ኤብለሉዋ፣ አንቺም ልጄ ነሽ። አልሃጂ ሙሳ በጣም ሀብታም ሰው ነው! የምትፈልጊውን ሁሉ ይሰጥሻል።››
‹‹ባባ ገንዘቡን አልፈልግም! ትምህርት ቤት መሄድ እፈልጋለሁ!››
አባቷ ‹‹ከሚቀጥለው የወር አበባሽ በፊት ታገቢዋለሽ›› አለና ከቤት ወጣ።
እድሏ ሲቃና አድራሻቸው ገበያ አጠገብ ስለነበር እዚያ ሄዳ ሁሉንም ነገር ነገረቻቸው። የእሷ ጉዳይ አሳስቧቸው ስለነበር ጠበቃ ቀጠሩላት።
ጠበቃውም አባቷ ትምህርት እንድትማር ካልፈቀደላት ፍርድ ቤት ክስ እንደሚያቀርብበት አስጠነቀቀው፡፡
ጠበቃው በግዳጅ ጋብቻ አለመፈጸሟንም አረጋገጠ።
ኤብላ ትምርቷን ጀመረች፡፡ ከክፍሏም አንደኛ ለመሆን ቻለች። በዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ለመማር የትምህርት ዕድል አገኘች።
አባቷ በጣም ኮራባት፡፡እና ዕድሏን እንዳታሳካ በመከልከሉ ተጸጸተ።
ዛሬ ኤብላ እሷ በነበረችበት ሁኔታ ውስጥ ያሉ ወጣት ልጃገረዶችን የምትረዳ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነች።
እያንዳንዷ ልጃገረድ እንደማንኛውም ወንድ ልጅ አስፈላጊ እንደሆነች እንድታውቅ ትፈልጋለች፡፡ ሁላችንም እኩል ነን!

