

አንድ ሎዲፖ የሚባል ሰው ነበር።
አካይ እና አኪቴላ ከሚባሉ ሁለት ሚስቶቹ ጋር ይኖር ነበር።
የሎዲፖ የመጀመሪያ ሚስት አካይ ዓይነስውር እናቱን የምታግዛቸው ብቻዋን ነበር።
አንድ ቀን የሎዲፖ ትንሿ ሚስት አኪቴላ ለባሏ ‹‹ወደ ደህና ቦታ እንሂድ እንጂ›› አለችው፡፡
የሚኖሩበት ቦታ በከብት ዘራፊዎች በየጊዜው ይጠቃ ነበር። አኪቴላ ደህንነቷ አደጋ ላይ መሆኑ ገባት።
ሎዲፖ ማየት የተሳናቸው እናቱ መንቀሳቀስ እንደማይፈልጉ ለአኪቴላ ነገራት። አኪቴላ የሎዲፖን እናት ትተው መሄድ እንዳለባቸው ተናገረች።
‹‹በቃ ከዚህ ካልተንቀሳቀስን ወደ ወላጆቼ እመለሳለሁ›› ስትል አኪቴላ ለሎዲፖ በጩኸት ተናገረች።
ሎዲፖ አኪቴላን በጣም ስለሚወዳት በፍላጎቷን ተስማማ። ለመሄድ ተዘጋጁ።
የመጀመሪያዋ ሚስቱ አካይ ግን ይህን ሁሉ ነገር ግራ በመጋባት ተመልክታለች።
የሎዲፖ ዓይነ ስውር እናት ከዛፉ ሥር ባለው የፍየል ቆዳ ላይ ተቀምጠዋል። ምን እየተካሄደ እንዳለ አያውቁም ነበር።
‹‹እንዴት ብቻቸውን እንተዋቸዋለን?›› በማለት አካይ ተገረመች።
ሎዲፖ እና ሚስቶቹ ንብረታቸውን በሙሉ በሁለት ግመሎቻቸው ላይ ጫኑ። አሮጊቷን እንኳን ሳይሰናበቷቸው በጸጥታ ስፍራውን ትተው ሄዱ።
አማቷን ብቻቸውን ትታቸው በመሄዷ አካይ እያለቀሰች ነበር።
አሮጊቷ ልጃቸውን እየጠሩ ይህን አሳዛኝ መዝሙር ዘመሩ፡፡ ማን ይንከባከበኛል ብለው ተጨነቁ።
ፀሐዩ ሲያቃጥለኝ ማን ወደ ጥላ ያደርገኛል ብለው አሰቡ።
ሎዲፖ እና ሚስቶቹ እንደሄዱ ወዲያውኑ ወራሪዎች መንደሩን አጠቁ።
ወራሪዎቹ አሮጊቷን ሴት ልጃቸው የት እንደሄደ እንዲነግሯቸው ጠየቋቸው። ‹‹ልንገድለው ስለሆነ ልንከተለው ነው›› በማለት ነገሯቸው።››
የመጀመሪያ ሚስቱንና ልጆቹን አትግደሉ ብለው ተማጸኑ። ሎዲፖ የወሰደውን በጋቸውን እንዲመልሱላቸውም ጠየቋቸው።
ተዋጊዎቹ ሎዲፖን ተከተሉት። ልክ በአዲሱ ቦታ እንደተቀመጠ አገኙት።
እሱንና ወጣቷን ሚስቱንም ገደሏቸው።
የመጀመሪያዋ ሚስቱ አካይ በጉን ይዛ ተመለሰች።
በደስታም አብረው ኖሩ።

