አንድ ቀን ጥንቸል ቀንድ አውጣ አገኘ። ቀንድ አውጣውንም ‹‹መሮጥ አትችልም! የምታውቀው ነገር መሬት ላይ መሳብ ብቻ ነው›› አለው።
ቀንድ አውጣውም ‹‹እሁድ መጥተህ እይ›› አለው።
ቀንድ አውጣው መቶ ወረቀቶች አዘጋጅቶ ሁሉም ላይ ተመሳሳይ መልዕክት ጻፈባቸው።
ቀንድ አውጣው ወረቀቱን ለጓደኞቹ ሰጣቸውና ‹‹ጥንቸሉ እኔን ፈልጎ እየተጣራ ወደዚህ ሲመጣ ከመካከላችሁ አንዱ ቀንድ አውጣው እኔ ነኝ ይበል›› አላቸው።
ከዚያም ቀንድ አውጣው ጥንቸሉ እና እሱ ከሚያልፉባቸው ቁጥቋጦዎች በስተጀርባ እንዲደበቁ ለጓደኞቹ ነገራቸው።
እሁድ እለት ጥንቸሉ መጥቶ ቀንድ አውጣውን አገኘው። ጥንቸሉም ‹‹በል እስኪ ውድድሩን እንጀምር። እኔ ግን አሸንፋለሁ›› አለው።
ቀንድ አውጣዎች ከዛፎች ጀርባ ተሰልፈው ስለነበር ጥንቸሉ ባለፈ ቁጥር እያንዳንዱ ቀንድ አውጣ ‹እኔ ነኝ ቀንድ አውጣው› እያለ ይጮህበታል፡፡ ጥንቸሉም ውድድሩን እያደረገ ‹‹ቀንድ አውጣ፣ ቀንድ አውጣ ›› እያለ ይጮሃል።
ከቁጥቋጦዎቹ በስተጀርባ ከተደበቁት ቀንድ አውጣዎች አንዱ ‹‹እኔ ቀንድ አውጣው ነኝ! እኔ ቀንድ አውጣው ነኝ!›› በማለት መለሰ፡፡
በመጨረሻም ጥንቸሉ በጣም ደከመው፡፡ ከዚያም‹‹በጣም ደክሞኛል፤ በቃ ቀንድ አውጣ አሸንፈኸኛል›› ብሎ ተኛ። አንድ ቀንድ አውጣ ከቁጥቋጦው ጀርባ ሆኖ የጥንቸሉን ድርጊት ይመለከት ነበር።
ስለዚህ ቀንድ አውጣው ጎበዝ ስለነበር ውድድሩን አሸነፈ፡፡